Loading
Singer
Updated 5d ago
አምላኬ ፡ ሆይ ፡ ቃሌን ፡ ስማ ፀሎቴን ፡ አድምጥ ፡ ልመናዬ ፡ ይድረስልኝ አንዴ ፡ አስበኝ ፡ ናልኝ ፡ አስበኝ በአንተ ፡ ብቻ ፡ ተስፋ ፡ አለኝ አንዴ (፪x) ፡ አስበኝ ሌላ ፡ ጥያቄ ፡ መሻት ፡ የለኝ ፀጋህ ፡ ሳያንሰኝ ፡ ምህረትሀ ፡ ሳይጎድል ምነው ፡ መዛሌ ፡ ምነው ፡ መታለል መንገድህ ፡ ባይሆን ፡ እንደመንገዴ እድልን ፡ ስጠኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x) አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x) አትሰብር ፡ ከቶ ፡ ቅጥቅጥ ፡ ሸምበቆ መንፈሱ ፡ ደቆ ፡ ሰው ፡ ካንተ ፡ ርቆ አታጠፋውም ፡ ሚጤሰውን ፡ ጧፍ ግን ፡ ሳታስበኝ ፡ ጊዜው ፡ እንዳያልፍ አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x) አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x) አሀአሀሀሀ ፡ አስበኝ አሀአሀሀ ፡ አስበኝ አስበኝ ፡ ጌታ ፡ አሀሀሀሀ ከአለት ፡ ንቃቃት ፡ ተሸሽጌያለሁ ክረምቱ ፡ ሲያልፍ ፡ ያኔ ፡ ወጣለሁ ለምትል ፡ ነፍሴ ፡ ለተጨነቀች የአንተን ፡ ጉብኝት ፡ አንዴ ፡ ትላለች አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x) አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x) ያለቦታዬ ፡ ቦታን ፡ አግኝቼ በምድያም ፡ ሀገር ፡ ሰውን ፡ ፈርቼ ተነስ ፡ የሚል ፡ ድምፅ ፡ አንተ ፡ ፅኔ ፡ ሀያል ስታስብ ፡ እንጂ ፡ ከየት ፡ ይሰማል አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x) አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x) አስበኝ ፡ እንደቃልህ አሀሀሀ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ እኔን ፡ አንዴ ፡ አስበኝ አትሰብር ፡ ከቶ ፡ አስበኝ መንፈሱ ፡ ደቆ ፡ እንደቃልህ አታጠፋውም ፡ አምላኬ ፡ ሆይ ግን ፡ ሳታስበኝ ፡ ጊዜው ፡ እንዳያልፍ አዝ፦ አስበኝ ፡ አስበኝ ፡ አንዴ ፡ አስበኝ (፪x) አሳልፈህ ፡ ለፈቃዴ ፡ ከቶ ፡ አትስጠኝ (፪x)