Loading
Singer
የፀጋ ፡ የምህረት ፡ ዘመኑ ፡ አብቅቶ ብርሃን ፡ ተሰውሮ ፡ የጥሪው ፡ ቀን ፡ መሽቶ ሰማያት ፡ ተፈተው ፡ ምድር ፡ ሳትናውጥ በነበልባል ፡ እሳት ፡ ጌታም ፡ ሳይገለጥ አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም አብሮ ፡ ደስ ፡ ይበለን ፡ ትንሽ ፡ ቆይ ፡ ስትልህ ዓለም ፡ በለዘብታ ፡ እያባበለችህ ተደላ ፡ ትካዜና ፡ ቁጭትን ፡ ጠብቆ ሲዖል ፡ እንዳትገባ ፡ ሳታስበው ፡ ከቶ አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም የእግዚአብሔር ፡ ነገር ፡ ለፍጥረታዊ ፡ ሰው ሊገባው ፡ አይችልም ፡ ፍፁም ፡ ሞኝነት ፡ ነው ፍጥረታዊውን ፡ ሥጋ ፡ መንፈሱ ፡ ሲሽረው ያኔ ፡ ትረዳለህ ፡ መንገዱ ፡ ጥበብ ፡ ነው አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም በመንታ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ሆነህ ፡ ስታማርጥ ፈጽሞ ፡ ላትረካ ፡ መንገድ ፡ ስትለዋውጥ ሞት ፡ ጥላውን ፡ ጥሎ ፡ አፍኖ ፡ ሳይወስድህ ጌታን ፡ ተቀበለው ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የሚያረካህ አዝ፦ አስብበት ፡ ዛሬ ፡ ነገን ፡ አትጠብቅ ራስህን ፡ ስትደልል ፡ ዘመንህም ፡ አይለቅ ሕይወት ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ ሌላስ ፡ አታገኝም አምነህ ፡ ድነህበት ፡ ታተም ፡ ለዘለዓለም