Loading
Singer
ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው በአለት ፡ ነው ፡ በአሸዋ ፡ ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው (፪x) ቤቴ ፡ አሸዋ ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው እስከአሁን ፡ ሰላም ፡ ነው ፡ ችግርም ፡ አላየሁ በጋው ፡ ተስማምቶኛል ፡ ምን ፡ ችግር ፡ ይመጣል ውኃ ፡ እኮ ፡ በአሸዋ ፡ ወዲያው ፡ ይመጠጣል "መስሎሃል" ይልቅ ፡ ወጪ ፡ አታውጡ ፡ አለት ፡ አትቧጥጡ ወጪን ፡ ይቀንሳል ፡ አሸዋ ፡ እኮ ፡ ሞልቷል የእኔስ ፡ ቤት ፡ አምራለች ፡ በጣም ፡ ዘንጣለች ላለሁበት ፡ ጊዜ ፡ ተመችታኛለች "ተው ፡ ይቅርብህ" አሸዋ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት (፪x) ፡ አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት አሸዋ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት (፪x) ፡ አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት ክረምት ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ዝናብ ፡ የመጣ ፡ ቀን ጐርፉ ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ንፋስ ፡ የመጣ ፡ ቀን ጠራርጐ ፡ ይወስደዋል ፡ አንዱንም ፡ ሳያስቀር ገንዘብህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት ዕውቀትህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት ሥልጣንህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት ጥበብህ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት አቤት ፡ ጉድ ፡ ፈላበት ችግር ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ሃዘን ፡ የመጣ ፡ ቀን መከራ ፡ የመጣ ፡ ቀን ፤ ማጣት ፡ የመጣ ፡ ቀን ጠራርጐ ፡ ይወስደዋል ፡ አንዱንም ፡ ሳያስቀር ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ባለት ፡ ነው ፡ በአሸዋ ፡ ቤትህ ፡ በምን ፡ ላይ ፡ ነው (፪x) ቤቴ ፡ በዓለት ፡ ላይ ፡ ነው ፡ የተመሠረተው ችግሩም ፡ በሽበሽ ፡ ነው ፡ መከራብ ፡ ብዙ ፡ ነው ጐርፉ ፡ ሲወርድብኝ ፡ ነፋስ ፡ ሲነፍስብኝ አለት ፡ ላይ ፡ ስላለሁ ፡ ቤቴ ፡ አልፈረሰብኝ "ኧረ ፡ ምንም ፡ አትሆን" አለት ፡ በቀላሉ ፡ አይገኝም ፡ ሲሉ የምደክም ፡ መስሎኝ ፡ ድሮ ፡ ተሞኘሁኝ የአሸዋ ፡ ነጋዴው ፡ ነበርና ፡ ወሬው ቤቴን ፡ በዓለት ፡ ብቻ ፡ ሰራሁ ፡ ከነአካቴው "ደግ ፡ አድርገሃል" አለቱ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት አለቱ ፡ ከሆነ ፡ የቤትህ ፡ መሠረት በቃ ፡ አለፈለት (፪x) ክረምቱ ፡ ቢመጣ ፤ ዝናቡም ፡ ቢወርድ ጐርፉ ፡ ቢንደረደር ፤ ንፋሱም ፡ ቢነፍስ የአንተ ፡ ቤት ፡ እንደሆን ፡ ፈጽሞ ፡ አይላወስ ኢየሱስ ፡ ከሆነ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት ቃሉ ፡ ከሆነልህ ፡ የሕይወትህ ፡ መሠረት በቃ ፡ አለፈለት (፪x) መከራ ፡ ቢመጣ ፤ ችግር ፡ ቢደርስብህ ሃዘን ፡ ቢያጋጥምህ ፤ ማጣት ፡ ቢያስቸግርህ አትነቃነቅም ፡ አለት ፡ ላይ ፡ ስላለህ አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ያየሁት ፡ በስጋ ፡ ዓይን ፡ አይደለም ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ በሕይወቴ ፡ አይቼዋለሁ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲዳስሰኝ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ያየሁት ፡ በስጋ ፡ ዓይን ፡ አይደለም ፡ ግን ፡ እርግጠኛ ፡ ነኝ በሕይወቴ ፡ አይቼዋለሁ ፡ ፍቅሩ ፡ ሲዳስሰኝ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) አለቱ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x) ኢየሱስ ፡ ነው ፡ መሠረቴ (፬x)