Loading
Singer
Updated 5d ago
ጓዳዬ ፡ ሆኜ ፡ የልቤን ነገርኩት ፡ የውስጥ ፡ የሆዴን በጊዜው ፡ ጌታ ፡ መጣና አሳመረልኝ ፡ ድንቅ ፡ አረገና (፪x) አሳመረለኝ ፡ አሃሃ ፡ ድንቅ ፡ አረገና (፪x) አሳመረልኝ ፡ አዎ ፡ ድንቅ ፡ አረገና (፪x) ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የራራልኝ ፡ የራራልኝ ያንን ፡ ዘመን ፡ ያሻገረኝ ፡ ያሻገረኝ ዘምራለሁ ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ያረገልኝ ፡ ብዙ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ውለታ ይዤ ፡ ልግባ ፡ ማደሪያው ምሥጋናዬ ፡ ያውድ ፡ መዓዛው ያውድ ፡ መዐዛው ፡ ይብዛ ፡ ዕልልታው (፪x) በማደሪያው ፡ ምሥጋናው በማደሪያው ፡ ዕልልታው በመቅደሱ ፡ ምሥጋናው በመቅደሱ ፡ ዕልልታው አላስኬድ ፡ ያሉኝ ፡ ከፊቴ ፡ ቆመው ህልሜን ፡ ተስፋዬን ፡ ሁሉ ፡ አጨልመው መንገዴን ፡ ዘግተው ፡ በቆሙት ፡ ላይ ቁጣው ፡ ነደደ ፡ መጣ ፡ ከላይ በበቀል ፡ እሳት ፡ ወረደባቸው ግድብ ፡ እንዲፈርስ ፡ አፈረሳቸው አፈረሳቸው (፪x) እኔማ ፡ ጌታን ፡ ብዬ አላፈርኩ ፡ እርሱን ፡ ብዬ ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ (፪x) ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ (፪x) ለእንቆቅልሼ ፡ መፍትሄ ፡ ሰጥቶ የሚያስፈነድቅ ፡ የልብን ፡ ሞልቶ ከአፉ ፡ ከወጣ ፡ ስልጣን ፡ ያለው ፡ ቃል የማይሆን ፡ የለም ፡ ያለው ፡ ይሆናል እንደርሱ ፡ ማነው ፡ ተዐምረኛ እንቆቅልሼን ፡ ፈቶ ፡ አሳየኛ ፈቶ ፡ አሳየኛ (፪x) ተሰርቶልኝ ፡ ስራዬ ሃዘን ፡ ሄዷል ፡ ከላዬ ቤቴን ፡ ሞላው ፡ ደስታ ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x) ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፬x) ፍጥረት ፡ በስራህ ፡ የሚገዙለት ማዕበል ፡ ወጀቡ ፡ የሚታዘዙለት ይናገር ፡ እንጁ ፡ ይበል ፡ ንጉሡ ማይሰማው ፡ የለም ፡ ሕያው ፡ ግዑዙ እርሱ ፡ ነው ፡ ጌታ ፡ ዐይኔ ፡ አይቶታል ማይቻለውን ፡ ሁሉ ፡ ችሎታል ሁሉ ፡ ችሎታል (፪x) እኔማ ፡ ጌታን ፡ ብዬ አላፈርኩ ፡ እርሱን ፡ ብዬ ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ (፪x) ጨመረ ፡ ምሥጋናዬ ተሰርቶልኝ ፡ ስራዬ ሃዘን ፡ ሄዷል ፡ ከላዬ ቤቴን ፡ ሞላው ፡ ደስታ ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፪x) ልዘምር ፡ ለዚህ ፡ ጌታ (፰x)