Loading
Singer
አዝ፦ አቀላልቷል ፡ ሰማዩ ፡ ሊሰናበት ፡ ሌቱ ምን ፡ ጭጋጉ ፡ ቢያይል ፡ አይቀርም ፡ መንጋቱ ብርሃን ፡ ዘንበል ፡ ቢል ፡ ቢዳምን ፡ ደመና አዲስ ፡ ቀን ፡ ያሳያል ፡ ጌታ ፡ ቸር ፡ ነውና (፪x) አሃሃ ፡ አንተን ፡ ታምኖ ፡ ማንስ ፡ ወድቆ ፡ ቀርቷል አሃሃ ፡ የታመነህ ፡ ሁሉን ፡ ጥሶ ፡ አልፏል አሃሃ ፡ መመኪያ ፡ ነህ ፡ ለምስኪኑ ፡ ጋሻ አሃሃ ፡ ማምለጫ ፡ ነህ ፡ ከጥፋት ፡ መሸሻ የእኔ ፡ አባት ፡ የእኔ ፡ ጌታ የእኔ ፡ ንጉሥ ፡ የእኔ ፡ አለኝታ በድካሜ ፡ ያልሳቅክብኝ ፡ እምባዬንም ፡ ያበስክልኝ ሳጸለቸኝ ፡ ተሸከምከኝ ፡ ከእናት ፡ ከአባት ፡ በላይ ፡ ሆንከኝ ኢየሱስ (፫x) ፡ ከፍ ፡ በልልኝ (፪x) አባት ፡ አለኝ ፡ እኔ ፡ ከአባትም ፡ አባት ያዋጣኛል ፡ ብዬ ፡ ያላፈርኩበት ፤ ያላፈርኩበት (፪x) እግዚአብሔር ፡ ከአየልኝ ፡ ከቶ ፡ አንድም ፡ አይጐድልም አምላኬ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ሁኔታን ፡ አላይም እጠብቀዋለሁ ፡ በስፍራዬ ፡ ሆኜ ያለውን ፡ ያደርጋል ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ጌታዬ እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሆናል እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይጸናል እግዚአብሔር ፡ ያለው ፡ ይሳካል (፪x) አዝ፦ አቀላልቷል ፡ ሰማዩ ፡ ሊሰናበት ፡ ሌቱ ምን ፡ ጭጋጉ ፡ ቢያይል ፡ አይቀርም ፡ መንጋቱ ብርሃን ፡ ዘንበል ፡ ቢል ፡ ቢዳምን ፡ ደመና አዲስ ፡ ቀን ፡ ያሳያል ፡ ጌታ ፡ ቸር ፡ ነውና (፪x)