Loading
Singer
አቀበት ፡ ሜዳ ፡ ገደላ ፡ ገደል የታለፈበት ፡ የሚረሳ ፡ አይደል ነዳፊው ፡ እባብ ፡ ነካሹ ፡ አውሬ ስንት ፡ አስረገጠኝ ፡ በዚህ ፡ በእግሬ የሠማይ ፡ አምላክ ፡ አቤት ፡ ምህረቱ ማድረግ ፡ ይችላል፡ ደካማን ፡ ብርቱ በእርሱ ፡ ሆናችሁ ፡ ያያችሁ ፡ ብዙ በዕልልታ ፡ ሆታ ፡ ምሥጋናን ፡ አብዙ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ መካሪ ፡ ወንድም ፡ ወላጅ ፡ አባቴ የሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ ቆርቁሮኝ ፡ አያውቅ ፡ ጠባይ ፡ አመሉ ጣቱን ፡ በመያዝ ፡ ዳዴ ፡ ተምሬ ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ ሆኖልኝ ፡ ዛሬ የጥንቱ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ ዛሬም ፡ ላክብረው ፡ በአንደበቴ ይሄ ፡ ክፉ ፡ ዓለም ፡ ምኑ ፡ ይመቻል በሥጋ ፡ በደም ፡ የትኛው ፡ ሲቻል በየማለዳው ፡ አዲስ ፡ በሆነው በምህረቱ ፡ ነው ፡ ያልጠፋነው እንደ ፡ እኔ ፡ ቢሆን ፡ እንደድካሜ ዛሬም ፡ በፊቱ ፡ ባልታየሁ ፡ ቆሜ በዓይኔ ፡ እያየሁት ፡ አለፈ ፡ ስንቱ የያዘኝ ፡ አምላክ ፡ እግዚአብሔር ፡ ብርቱ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ መካሪ ፡ ወንድም ፡ ወላጅ ፡ አባቴ የሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ ቆርቁሮኝ ፡ አያውቅ ፡ ጠባይ ፡ አመሉ ጣቱን ፡ በመያዝ ፡ ዳዴ ፡ ተምሬ ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ ሆኖልኝ ፡ ዛሬ የጥንቱ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ ዛሬም ፡ ላክብረው ፡ በአንደበቴ ይህን ፡ ዮርዳኖስን ፡ ስሻገረው ደረቅ ፡ በትር ፡ ነው ፡ በእጄ ፡ የነበረው ዛሬ ፡ ግን ፡ ይሄው ፡ ዓለመለኝ በተዓምራቱ ፡ እያስገረመኝ ሕይወት ፡ ዥንጉርጉር ፡ ቀለሙ ፡ ብዙ መች ፡ ቀላል ፡ ሆነ ፡ ጓዙ ፡ መዘዙ የሰበሰበኝ ፡ የያዘኝ ፡ ጌታ ስሙ ፡ ከፍ ፡ ይበል ፡ በዕልልታ ፡ ሆታ አዝ፦ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ መድሃኒቴ መካሪ ፡ ወንድም ፡ ወላጅ ፡ አባቴ የሆነልኝ ፡ ሁሉ ፡ በሁሉ ቆርቁሮኝ ፡ አያውቅ ፡ ጠባይ ፡ አመሉ ጣቱን ፡ በመያዝ ፡ ዳዴ ፡ ተምሬ ቆሜ ፡ ለመሄድ ፡ ሆኖልኝ ፡ ዛሬ የጥንቱ ፡ አምላክ ፡ የልጅነቴ ዛሬም ፡ ላክብረው ፡ በአንደበቴ