Loading
Singer
አንተው ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መታመኛ አንተው ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ መደገፊያ (፪x) እግዚአብሔር ፡ ትክክል ፡ ነው ፡ ነገር ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው ማን ፡ ይቀራል ፡ እንባው ፡ ፈሶ ፡ ይታበሳል ፡ ቀኑ ፡ ደርሶ መታመኛው ፡ እግዚአብሔር ፡ ማረፊያውም ፡ ከጥላው ፡ ሥር በኩፉ ፡ ቀናት ፡ ከጐኑ ፡ ሆኖለታል ፡ በዘመኑ አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x) ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x) እንዳተ ፡ ያለ ፡ መልካም ፡ ለሰው ፡ የሚራራ የተዋረደውን ፡ ደርሶ ፡ የሚያኮራ አላገኘሁም ፡ እኔስ ፡ እስከ ፡ እድሜዬ ፡ ልክ እወድሃለሁኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የኔ ፡ አምላክ አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x) ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x) ቅዱስ ፡ ሥሙ ፡ እንዲጠራ ፡ ትልቅ ፡ ታሪክ ፡ በእኔ ፡ ሰራ ጠላቶቼን ፡ አሳፍሮ ፡ ታየ ፡ ጌታ ፡ በኔ ፡ ከብሮ አልቀረሁም ፡ እንደወደቅኩ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ መቼ ፡ አፈርኩ አጥር ፡ ቅጥሩን ፡ እየዘለልኩ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩ አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x) ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x) አቅም ፡ ጉልበት ፡ ስለሌለው ፡ የት ፡ ይደርሳል ፡ የተባለው ዛሬ ፡ ታዲያ ፡ ለዚህ ፡ ክብር ፡ ለዚህ ፡ ሹመት ፡ ማን ፡ አበቃው ጌታ ፡ እኮ ፡ ነው ፡ የእርሱ ፡ ተስፋ ፡ መድረሻ ፡ አለው ፡ እንዳይጠፋ ያግዘዋል ፡ የታመነው ፡ ያኮራዋል ፡ የሚያመልከው አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x) ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x) ቅዱስ ፡ ሥሙ ፡ እንዲጠራ ፡ ትልቅ ፡ ታሪክ ፡ በእኔ ፡ ሰራ ጠላቶቼን ፡ አሳፍሮ ፡ ታየ ፡ ጌታ ፡ በእኔ ፡ ከብሮ አልቀረሁም ፡ እንደወደቅኩ ፡ ጌታን ፡ ይዤ ፡ መቼ ፡ አፈርኩ አጥር ፡ ቅጥሩን ፡ እየዘለልኩ ፡ እኖራለሁ ፡ እያመለኩ አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x) ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x) እንዳንተ ፡ ያለ ፡ መልካም ፡ ለሰው ፡ የሚራራ የተዋረደውን ፡ ደርሶ ፡ የሚያኮራ አላገኘሁም ፡ እኔስ ፡ እስከ ፡ እድሜዬ ፡ ልክ እወድሃለሁኝ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የእኔ ፡ አምላክ አዝ፦ አንተው ፡ ነህ ፡ ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፪x) ጌታዬ ፡ መተማመኛዬ (፬x)