Loading
Singer
አመታት አለፉ ዘመናትም ሄዱ እስካሁን በቤቱ አለሁኝ እያገለገልኩኝ/ገና እኖራለሁኝ በቤትህ ተተክዬ እንዳፈራልህ ታማኝ ባሪያ ሆኜ እንድኖርልህ ለኔ ምኞቴ ነው ቀን ከሌት ፀሎቴ በክብር እስክገባ የላይኛው ቤቴ አሜን/*8 እንደዚያች ውርንጫ በላዬ ተቀምጠህ ስራ ስትሰራብኝ ታሪኬን ለውጠህ ይህንን የሰማ ዲያብሎስ ቢቀና ወዴት ያገኘኛል ዛቻው ሁሉ መና አሜን/*4 በድካም በብርታት በመውደቅ መነሳት ከክፉ ውሳኔ ነፍሴን ስትመልሳት ብዙ ጊዜ አየሁህ ጣልቃ ስትገባ ድርሰህ ስታድነኝ ከጠላት ከበባ ያኔ ካንተ ጋራ ጉዞ የጀመሩ አሉ ብዙ ሰዎች ከኋላ የቀሩ እኔ ይገርመኛል እስካሁን መቆሜ ፅዮን እስክገባ አንተው ነህ አቅሜ