Loading
መኖር ፡ አልችልም ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ (አሃሃሃ) አንተን ፡ ሳልጠራ ፡ ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ (ኦሆሆሆ) ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የማትጠገብ ፡ (አሃሃሃ) ይረካል ፡ ልቤ ፡ ሁሌ ፡ አንተን ፡ ሲያስብ ፡ (ኦሆሆሆ) አንተን ፡ ብቻ ፡ ሲያስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x) አያጓጓኝም ፡ ሌላው ፡ ነገር ቢሆንልኝም ፡ ወይም ፡ ቢቀር የምታረካኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ እጠግባለሁኝ ፡ ሁሌ ፡ ሳስብህ አያጓጓኝም ፡ የዓለም ፡ ነገር ቢሆንልኝም ፡ ወይም ፡ ቢቀር የምታረካኝ ፡ አንተ ፡ ብቻ ፡ ነህ እጠግባለሁኝ ፡ ሁሌ ፡ ሳስብህ አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x) በአይምሮዬ ፡ የምስለዉ በሕሊናዬ ፡ የማስበዉ ሰላም ፡ የሚሰጠኝ ፡ አንድ ፡ ነገር አንተን ፡ ማሰብ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x) አንተን ፡ ብቻ ፡ ማሰብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x) መኖር ፡ አልችልም ፡ መዋል ፡ ማደር ፡ (አሃሃሃ) አንተን ፡ ሳልጠራ ፡ በዚች ፡ ምድር ፡ (ኦሆሆሆ) ፍቅር ፡ እኮ ፡ ነህ ፡ የማትጠገብ ፡ (አሃሃሃ) ይረካል ፡ ልቤ ፡ ሁሌ ፡ አንተን ፡ ሲያስብ ፡ (ኦሆሆሆ) አንተን ፡ ብቻ ፡ ሲያስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፬x) ፍቅር ፡ የያዘኝ ፡ ከኢየሱስ ፡ ነዉ መች ፡ ከሚጠፋ ፡ ከሚያልፈዉ ምኞቴ ፡ የሆንክ ፡ አገኘሁህ አንተኑ ፡ ሳስብ ፡ አረፍኩብህ ፍቅር ፡ የያዘኝ ፡ ከጌታዬ ፡ ነዉ መች ፡ ከሚጠፋ ፡ ከሚያልፈዉ ምኞቴ ፡ የሆንክ ፡ አገኘሁህ አንተኑ ፡ ሳስብ ፡ አረፍኩብህ አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳስብ ፡ አንተን ፡ ብቻ (፪x) አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳመልክ ፡ አንተን ፡ ብቻ አንተን ፡ ብቻ ፡ ሳከብር ፡ አንተን ፡ ብቻ (፪x)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.