Loading
Singer
አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ በእምነት ፡ እሻገራለሁ በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ ከቀደሙት ፡ ተምሬያለሁ የአንተን ፡ ተስፋ ፡ እጠብቃለሁ በምሕረትህ ፡ ተመልከተኝ እምነትንም ፡ ጨምርልኝ አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ በእምነት ፡ እሻገራለሁ በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ የፍየልን ፡ ሌጦ ፡ ለብሰው መስቀልህን ፡ ተንተርሰው እየተንከራተቱ ፡ ብዙ ፡ አሉ ክብራቸውን ፡ ለአንተ ፡ የጣሉ አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ በእምነት ፡ እሻገራለሁ በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ በእምነት ፡ ሥምህን ፡ ጠሩ በፀሎት ፡ ለአንተ ፡ ነገሩ ከላይ ፡ ሆነህ ፡ ሰማሃቸው ቃላቸውን ፡ አደመጥካቸው አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ በእምነት ፡ እሻገራለሁ በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ በእምነት ፡ ባሕርን ፡ ከፈሉ ከጠላት ፡ እጅ ፡ አመለጡ እነርሱን ፡ ልመስል ፡ እሻለሁ በእምነት ፡ ሥምህን ፡ ጠራለሁ አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ በእምነት ፡ እሻገራለሁ በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ በመንፈስ ፡ መልዕክትን ፡ ሰሙ ጌታ ፡ አንተን ፡ ተሳለሙ እምነትን ፡ ስጠኝ ፡ እላለሁ እኔም ፡ አንተን ፡ ለምናለሁ አዝ፦ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ እኔን ፡ ወደ ፡ ኋላ ፡ ጥዬ በእምነት ፡ እሻገራለሁ በድል ፡ ፊትህን ፡ አያለሁ