Loading
Singer
ሰማያትን ፡ ሳይ ፡ ከዋክብትን የፀሐይ ፡ ድምቀት ፡ ግሩም ፡ ፍጥረትህ ምድርን ፡ ወብ ፡ አድርገህ ፡ ማበጃጀትህ አይጠገብም ፡ አቤት ፡ ጥበብህ አዝ፦ አንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ ለአንተ ፡ እዘምራለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ አእዋፍ ፡ በዛፎች ፡ ላይ ፡ ተደላድለው ፡ ሲያርፉ በማለዳ ፡ መዝሙር ፡ ሌሊቱን ፡ ሲገልጡ ብሩህ ፡ ልዩ ፡ ተስፋ ፡ ጥርት ፡ ባለው ፡ ሰማይ ትናንት ፡ ትናንት ፡ አልፎ ፡ አዲስ ፡ ቀን ፡ በቀን ፡ ላይ አዝ፦ አንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ የፍጥረት ፡ ቀለም ፡ ድብቅ ፡ ውበቱ የሰማይ ፡ ርቀት ፡ የምድር ፡ ስፋቱ ግሩም ፡ ድንቅ ፡ ቤት ፡ ለሰው ፡ መቆያ ጌታ ፡ ያዘጋጀህ ፡ መልካም ፡ ማደሪያ አዝ፦ አንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ስምረትን ፡ እያየሁ አድማስ ፡ ከሩቅ ፡ ሆኖ ፡ ፍጥረትን ፡ ሲታዘብ ደመና ፡ ከሰማይ ፡ አውቆ ፡ ሲሰበሰብ በዶፍ ፡ ዝናብ ፡ መሃል ፡ መብረቅ ፡ ሲያስተጋብ ፍጥረት ፡ ቤቱን ፡ አውቆ ፡ በስፍራው ፡ ሲገባ አዝ፦ አንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ ጊዜ ፡ ጊዜን ፡ ሲወልድ ፡ ወቅቱ ፡ ሲለዋወጥ መልካም ፡ ፍሬ ፡ አበባ ፡ አዲስ ፡ ዘር ፡ ሲገለጥ ጭጋጉ ፡ ደመናው ፡ በድንገት ፡ ተገፎ ፀሐይ ፡ ስትፈነጥቅ ፡ ወቅቱ ፡ በወቅት ፡ አልፎ አዝ፦ አንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ አንተን ፡ አመልካለሁ (፫x) ፡ ፍጥረትን ፡ እያየሁ በውድቅት ፡ ሌሊት ፡ ታይቶ ፡ የማይጠገብ ከዋክብት ፡ ሲያበሩ ፡ ግርማቸው ፡ ሲነበብ ሰማይ ፡ እንደ ፡ ድንኳን ፡ አምሮ ፡ ተዘርግቶ እንዴት ፡ ደስ ፡ ያሰኛል ፡ ማየት ፡ ምድርን ፡ ሞልቶ አዝ፦ አንተን ፡ አደንቃለሁ (፫x) ፍጥረትን ፡ እያየሁ ለአንተ ፡ ዘምራለሁ (፪x) ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ ፡ ሰማይን ፡ እያየሁ ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ኢየሱስ ፡ ሥምህ ፡ ከፍ ፡ ከፍ ፡ ይበል ። እንደ ፡ አንተ ፡ ያለ ፡ ማን ፡ አለ? ሃሌሉያ!