Loading
Singer
የሰማይ ፡ ብርሃን ፡ ጨለማውን ፡ ገፍፎ ሲዖል ፡ ድል ፡ ተነስቶ ፡ ሞትም ፡ ተሸንፎ በኃጢያት ፡ ተወግተው ፡ ደክመው ፡ ለወደቁ ጥሪው ፡ ያስተጋባል ፡ ሙታን ፡ እንዲነቁ አዝ፦ አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል ማየት ፡ በሌለበት ፡ መስማት ፡ በጠፋበት ምሬትና ፡ ፀፀት ፡ ለቅሶ ፡ ከሞላበት ምንድን ፡ ነው ፡ የጣለህ ፡ እንደምንስ ፡ መጣህ ከሕያዋን ፡ ምድር ፡ ፈጥነህ ፡ ለምን ፡ ወጣህ አዝ፦ አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል ከእንቅልፍ ፡ የምትነሳበት ፡ ሰዓት ፡ ነው ጊዜህን ፡ መርምረው ፡ ዘመኑን ፡ እወቀው እንግዲያውስ ፡ ንቃ ፡ ተነስ ፡ ተመላለስ አንተም ፡ ተመልሰህ ፡ የጠፉትን ፡ መልስ አዝ፦ አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል ድፍረትህን ፡ አትጣል ፡ ብድራት ፡ አለና በመንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ኃይል ፡ ተነስ ፡ እንደገና የደከመው ፡ እጅህ ፡ የዛለው ፡ ጉልበትህ ዳግም ፡ ተጠናክሮ ፡ ያፈራል ፡ ሕይወትህ አዝ፦ አንተ ፡ የምትተኛ ፡ ኢየሱስ ፡ ይጠራሃል በሰማዩ ፡ ፍቅር ፡ ይቀሰቅስሃል ከተሸሸግበት ፡ ከሙታን ፡ መቃብር ፡ ተነሳ ፡ ይልሃል