Loading
Singer
አንተ ሰባኪ ሆይ ስማኝ አንተ ሰባኪ ሆይ በያደባባዩ መዳንን - ላጣ ሰው ለማይሞላ ሆዱ - ተስፋን ስታጎርሰው አለምን መረጠ - ከኢየሱስ ስራ በወንጌል መጫሚያ - ንዋይ ስትጠራ አንተ ሰባኪ ሆይ ስማኝ አንተ ሰባኪ ሆይ አንድም ስንወድቅ ነው - አንድም ስንነሳ የኢየሱስ ስራ - በኛ የሚወሳ ትሾማለህ ብቻ - ትበላለህ ብቻ ማዳኑን አትተካ - በገንዘብ እንጎቻ [አዝ] የጠበቀህ እንዲሁ - 'ካስፈሪ ማዕበል ከልሎኝ ነቅ እንጂ - ሀይሌ ነው አትበል በእኔነት ካባ - አለባብሰው ቢያርሱ (ኃላ ለአረም ነው) የሚገልም እሱ - የሚያድንም እሱ [አዝ] አእላፋት በ'ጆችህ - ባ'ደራ ሲሰጡ አንተን ሊከተሉ - ከየጫፍ ቢመጡ ባውርቷ'ደር መሃል - ባ'ስመሳይ ጎዳና በኑሮህም አፅና - የቃልህን ዳና [አዝ]