Loading
Singer
ሰው ፡ እንዳለህ ፡ አይደለህም ፡ አእምሮ ፡ እንዳሰበህ ከመጣው ፡ ሁሉ ፡ ታልፋለህ ፡ ከተነገረልህ (፪x) ከሚሉህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ ጌታ ከሚሉህ ፡ በላይ ከሚሉህ ፡ በላይ ፡ ነህ ፡ አምላኬ ከሚሉህ ፡ በላይ (፪x) ብዙዎች ፡ አውቀናል ፡ እንዳሉ በራሳቸው ፡ አእምሮ ፡ እንዳሰሉ አንተ ፡ ግን ፡ እንደዛ ፡ አይደለህም ትልቅ ፡ ነህ ፡ ማንም ፡ አያውቅህም አስገረመኝና ፡ ሥራህ ማልጄ ፡ ተነሳሁ ፡ ላመልክህ ፈቃዴን ፡ ሰጠሁ ፡ እራሴን ግዛኝ ፡ ኢየሱሴ ግዛኝ ፡ ኢየሱሴ (፰x) አላፋው ፡ አግዳሚው ፡ እንዳለህ አውቀናል ፡ ብለው ፡ እንዳወሩ ሺህ ፡ ቃል ፡ ቢደረደር ፡ አይገልፅህ አምላኬ ፡ ከመባል ፡ ታልፋለህ በትላንቱ ፡ ነገር ፡ ስገረም ዛሬም ፡ አስደነቅከኝ ፡ ዳግም ተዓምራትህ ፡ በዛ ፡ በሕይወቴ አንተ ፡ ነህ ፡ አባቴ አንተ ፡ ነህ ፡ አባቴ (፲x) እስከመቼ ፡ ያልኩኝ ፡ ፍቺ ፡ ላጣው ፡ ህልሜ ምላሽን ፡ ሰጥቶኛል ፡ እንዳልቀር ፡ ደክሜ ጌታ ፡ ባየኝ ፡ ወራት ፡ እንዲህ ፡ ሆኖልኛል አንደበቴም ፡ ሁሉ ፡ ዛሬማ ፡ ምሥጋናን ፡ ያወራል ዘመርኩበት ፡ ባለቀስኩበት ዘመርኩበት ፡ አይሆንም ፡ ባልኩበት ዘመርኩበት ፡ ባጉረመረምኩበት ዘመርኩበት ፡ በጠላቶቼ ፡ ፊት (፫x) ምንም ፡ ታናሽ ፡ ቢሆን ፡ ጅማሬው ፡ የተነሳበት ፍፃሜው ፡ ትልቅ ፡ ነው ፡ በአምላኩ ፡ የሚደርስበት እጅህን ፡ አታንሳ ፡ በድፍረት ፡ ጌታ ፡ በገባው ፡ ላይ ስለ ፡ እርሱ ፡ ተዋጊ ፡ ተሟጋች ፡ አለና ፡ በሰማይ (፪x)