Loading
Singer
ላሞግሰው ፡ ዙፋንህን ፡ ላደናንቅ ከእግሮችህ ፡ ስር ፡ ሆኜ ፡ ቅኔን ፡ ላፈልቅ አንደበቴን ፡ ቀድሼ ፡ ዜማ ፡ ላፈስ ጌታ ፡ ልልህ ፡ መጣሁ ፡ ክበር ፡ ንገሥ እንዲህ ፡ ከሚሉ ፡ ጋራ ፡ ልተባበር እኔም ፡ የእራሴን ፡ ፈንታ ፡ ልጨምርልህ ይሄም ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ አይበዛምና ከናፍርቶቼ ፡ ይጥሩህ ፡ ብለው ፡ ገናና ፡ አንተ ፡ ገናና አንተ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ገናና (፪x) በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ ነህ በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x) ከሰማነው ፡ እና ፡ ካየነው በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚህም ፡ በላይ ፡ ነህ ከዘመርነው ፡ ከሰበክነው በላይ ፡ ነህ ፡ ከዚያም ፡ በላይ ፡ ነህ (፪x) የለም (፫x) ፡ ሌላ ፡ ጌታ ፡ የለም የለም(፫x) ፡ ሌላ ፡ ንጉሥ ፡ የለም የለም (፫x) ፡ ሌላ ፡ አዳኝ ፡ የለም የለም (፫x) ፡ ሌላ ፡ ገዢ ፡ የለም ሌላ ፡ ጌታ ፡ የለም ፣ ሌላ ፡ ንጉሥ ፡ የለም ሌላ ፡ አዳኝ ፡ የለም ፣ ሌላ ፡ ገዢ ፡ የለም (፪x) በእውነትና ፡ በመንፍስ ፡ ስትመለክ ፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ በፊትህ ፡ ሲል ፡ ዝቅ ፡ ዝቅ ቋንቋው ፡ ሁሉ ፡ ስለአንተ ፡ ዝና ፡ ሲያወራ ሲባል ፡ ከአማልክት ፡ ሁሉ ፡ ነህ ፡ የተፈራህ እንዲህ ፡ ከሚሉ ፡ ጋራ ፡ ልተባበር እኔም ፡ የእራሴን ፡ ፈንታ ፡ ልጨምርልህ ይሄም ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ለአንተ ፡ አይበዛምና ገና ፡ ፍጥሮችህ ፡ ይጥሩህ ፡ ብለው ፡ ገናና ፡ አንተ ፡ ገናና አንተ ፡ ገናና ፡ ነህ ፡ አንተ ፡ ገናና (፪x) በላይ ፡ በሰማይ ፡ ላለው ፡ በዙፋኑ ለሚገዙለት ፡ እልፍ ፡ ቅዱሳኑ ለሚባርኩ ፡ ስሙን ፡ በዝማሬ አምላክ ፡ ለሆነው ፡ ጥንትም ፡ ቢሆን ፡ ዛሬ (፪x) እኔም ፡ አለኝ ፡ አምልኮ እኔም ፡ አለኝ ፡ ምሥጋና እኔም ፡ አለኝ ፡ ዕልልታ በአመታት ፡ መካከል ጸንቶ ፡ ለሚኖረው ለጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x) ለጌቶቹ ፡ ጌታ ለነገሥታት ፡ ንጉሥ ለጌቶቹ ፡ ጌታ (፪x)