Loading
Singer
በተዘረጋ ፡ ክንድ ፡ በበረታችም ፡ እጅ በጌታ ፡ መዳኑን ፡ ከሞት ፡ ከሲዖል ፡ እጅ እንደምን ፡ ዘንግቶ ፡ ሰው ፡ ያጉረመርማል ወንድሙን ፡ ለመውገር ፡ እጁን ፡ ይዘረጋል አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥርሱን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) ስፍራውን ፡ ለቆ ፡ ሲሄድ ፡ ለመጉደፍ ፡ ሲቸኩል ትህትናውን ፡ አውልቆ ፡ ለሞት ፡ ሲንቀለቀል እዪት ፡ ያንን ፡ ዝንጉ ፡ ቃል ፡ ኪዳኑን ፡ ሲያፈርስ በአመጻው ፡ ብዛት ፡ ፍቅርን ፡ ሲያቀዘቅዝ አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x) አንተን ፡ እየፈራሁ ፡ ቀኑን ፡ ሁሉ ፡ ልኑር ትህትናም ፡ አይራቀኝ ፡ አልነፈግህ ፡ ክብር እጅህ ፡ እንዳይመታኝ ፡ አጉል ፡ ደፋር ፡ ሆኜ መተረቻ ፡ እንዳልሆን ፡ በሃፍረት ፡ ተከድኜ አዝ፦ ስጋ ፡ ነፍሱን ፡ ዘርቶ ፡ አመጽ ፡ አቆጥቁጦ ትህትና ፡ ተረስቶ ፡ የትዕቢት ፡ ኃይል ፡ ፈጦ ፍቅርን ፡ ገደል ፡ ከቶ ፡ ጥላቻን ፡ ለማንገሥ ጥፍሩን ፡ ይስል ፡ ጀመር ፡ ሰው ፡ ለመነካከስ አንተ ፡ ግን ፡ ጌታ ፡ ሆይ ፡ ምህረትህን ፡ አፍስስ (፪x)