Loading
Singer
እንዳልዳኑት በዘር ተከፍለው ዳግም መወለድን ረስተው ብዙዎች ከእውነት ተሳስተዋል በዘመኑ ነፋስ ተወስደዋል አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ (፪x) ዝናቡ ጎርፉ ሲመጣ ድንገት ሲገለጥ ያምላክ ቁጣ ፍጻሜህ ውድቀት እንዳይሆን ባለቱ ላይ ስራው ቤትህን አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ መልካሙን ነገር የማይወዱ በቅድስና የማይሄዱ ፍቅር የሌላቸው ትምክህተኞች የዘመኑ ማብቂያ ምልክቶች አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ ብዙዎች ነበሩ የተጠሩ ጌታን ሲያገኙ የከበሩ ጥቂት ሲቀረው ፍሬቸው እሾሁ ውጦ አስቀራቸው አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ አንዳንዶች ባለመትጋታቸው መሃል መንገድ ላይ ደከማቸው አንተም እንዳትቀር ወደ ኋላ ዘውትር ጸልይ ቃሉን ብላ አንተ ግን አማኝ እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ አንተ ግን እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ እስከ ምጻቱ ድረስ ሂድ እስከ ፍጻሜው ድረስ ሂድ