Loading
Singer
"እንዲህም ፡ አላቸው። 'ወደ ፡ ዓለም ፡ ሁሉ ፡ ሂዱ። ወንጌልንም ፡ ለፍጥረት ፡ ሁሉ ፡ ስበኩ።'" የማርቆስ ፡ ወንጌል ም. ፲፮ : ቁ.፲፭ አዝ፦ አንተ ፡ ባለአደራ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው አንተ ፡ መልዕክተኛ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው ተነስ ፡ መጽሓፉን ፡ አንሳ ፤ ተነስ ፡ ሚስጥሩን ፡ ግለጠው ተነስ ፡ ግራ ፡ ለተጋባው ፤ ተነስ ፡ ልቡን ፡ አሳርፈው (፪x) የሕይወትን ፡ መንገድ ፡ አሳየኝ ፡ እያሉ በጓዳቸው ፡ ሆነው ፡ ስንቶች ፡ ያለቅሳሉ ፡ አሄ አንተ ፡ በዳንክበት ፡ መዳን ፡ አስባቸው የእውነትን ፡ ቃል ፡ ይዘህ ፡ ሂድ ፡ ድረስላቸው ፡ እህ ፡ ሂድ ፡ ድረስላቸው ብድራትህን ፡ ትኩር ፡ ብለህ ፡ ተመልከትና የቀድሞው ፡ ነገር ፡ ትውስ ፡ ይበልህ ፡ እስኪ ፡ እንደገና ያኔ ፡ የነበረው ፡ ትኩስ ፡ ፍቅርህ ፡ ዛሬም ፡ ቢቀና ያቀናልሃል ፡ አምላክህ ፡ ደግሞ ፡ የአንተን ፡ ጐዳና አዝ፦ አንተ ፡ ባለአደራ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው አንተ ፡ መልዕክተኛ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው ተነስ ፡ መጽሓፉን ፡ አንሳ ፤ ተነስ ፡ ሚስጥሩን ፡ ግለጠው ተነስ ፡ ግራ ፡ ለተጋባው ፤ ተነስ ፡ ልቡን ፡ አሳርፈው (፪x) በሚብለጨለጨው ፡ ውበቷ ፡ ተማርከው ስንቶች ፡ ሲኦል ፡ ገቡ ፡ ከምድር ፡ ተስማምተው ፡ አሄ የሰማዩን ፡ ክብር ፡ የላዩን ፡ ሳያውቁ መቃብር ፡ ወረዱ ፡ ሃያላን ፡ አለቁ ፡ እህህ ፡ ጠቢባን ፡ አለቁ ወንጌሉን ፡ ይዘህ ፡ ሳትመሰክር ፡ ዘመን ፡ አለፈህ ሰዉ ፡ እንደቅጠል ፡ በቀን ፡ በማታ ፡ እየረገፈ መክሊቱን ፡ ቀብረህ ፡ ሳታተርፍበት ፡ ጌታ ፡ እንዳይመጣ የተሰጠህን ፡ አደራ ፡ ይዘህ ፡ ፈጥነህ ፡ በል ፡ ውጣ ፡ አሄ አዝ፦ አንተ ፡ ባለአደራ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው አንተ ፡ መልዕክተኛ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው የወንጌል ፡ አርበኛ ፡ ሆይ ፡ ወዴት ፡ ነው ፡ ያለኸው ተነስ ፡ መጽሓፉን ፡ አንሳ ፤ ተነስ ፡ ሚስጥሩን ፡ ግለጠው ተነስ ፡ ግራ ፡ ለተጋባው ፤ ተነስ ፡ ልቡን ፡ አሳርፈው (፪x)