Loading
Singer
ሰልፉ ፡ ተከማቸ ፡ ጦር ፡ ተወረወረ የወንጌሉን ፡ ዘማች ፡ ያዙልኝ ፡ ተባለ የሞት ፡ ጥላ ፡ ረዝሞ ፡ ለሰሚው ፡ ቢያስፈራም መጋደልን ፡ ለምደናል ፡ ለአምላካችን ፡ ስራ አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x) ስጋው ፡ ለመከራ ፡ ቁርበቱን ፡ ለአለንጋ አማኝ ፡ የሚያቀርበው ፡ ላመነበት ፡ ዋጋ እንደዚህ ፡ ከሆነ ፡ አምላክ ፡ ይሁን ፡ ያለው እንኳንስ ፡ መከራ ፡ ይሁን ፡ የፈቀደው አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x) የመድህኑን ፡ ተስፋ ፡ ባይገነዘቡ ስለ ፡ ሽልማቱ ፡ መዋረድ ፡ ኮከቡ አምላክ ፡ ባይኖርለት ፡ ተረስቶ ፡ ነበር ትላንት ፡ የታደገው ፡ ዛሬም ፡ በእርግጥ ፡ አለ አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x) በስጋችን ፡ ፈርደን ፡ በነፍስ ፡ ቆርጠናል የደህንነት ፡ ጉዞ ፡ አንዴ ፡ ጀምረናል ወድቀንም ፡ ተነስተን ፡ ይህን ፡ ሁሉ ፡ ስናልፍ በድል ፡ እንዘጋለን ፡ የሕይወትን ፡ ምዕራፍ አዝ:- አንዴ ፡ ቆርጠናል ፡ ተከትለናል በእምነት ፡ ጀምረን ፡ በድል ፡ እናከትማለን (፪x)