Loading
Singer
አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ ሁሉን ፡ ወደምትችል ፡ ወደአንተ ፡ እጮሃለሁ ልትረዳኝ ፡ እንደምትችል ፡ ይህንን ፡ አውቃለሁ በወደድከው ፡ መንገድ ፡ ጌታ ፡ ተናገረኝ ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ ብቻ ፡ አንድ ፡ ነገር ፡ አባ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ ሙግቴ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ መሆኑን ፡ ስታውቀው ለምን ፡ ዝም ፡ እንዳልከኝ ፡ ያልገባኝ ፡ ሚስጥር ፡ ነው ተናገረኝ ፡ ጌታ ፡ ያየኸው ፡ ጉድለቴን አንተ ፡ ዝም ፡ ካልክማ ፡ ሌላ ፡ ማነው ፡ ያለኝ አንተ ፡ ዝም ፡ ካልክማ ፡ ሌላ ፡ ማንም ፡ የለኝ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ አንተ ፡ ዝም ፡ ባልክበት ፡ በካህኑ ፡ ኤሊ ፡ ዘመን ድል ፡ አይታወቅም ፡ ሁሌ ፡ መሸነፍ ፡ ነው እስከ ፡ ሲዖል ፡ ድረስ ፡ ነፍስን ፡ ያወርዳታል የአንተ ፡ ዝምታ ፡ ነፍሴን ፡ ያሰጋታል (፪x) አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈራው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምሰጋው አንተ ፡ ዝም ፡ ስትለኝ ፡ ነው (፪x) እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ዝም ፡ አትበለኝ መልሰህ ፡ መላልሰህ ፡ ብትናገረኝም ማስተዋል ፡ ቢያቅተኝ ፡ ተው ፡ አትሰልቸኝ በአባትነት ፡ ፍቅርህ ፡ በልምጭ ፡ ሾጥ ፡ አርገኝ ዝም ፡ ካልከኝማ ፡ አባ ፡ ዋጋም ፡ የለኝ ዝም ፡ ካልከኝማ ፡ ኢየሱስ ፡ ዋጋም ፡ የለኝ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምረካው አንተ ፡ ስትናገረኝ ፡ ነው (፪x) አንድ ፡ ነገር ፡ በሕይወቴ ፡ የምፈታው አንተ ፡ ስትናገረኝ ፡ ነው (፪x) እባክህ ፡ ተናገረኝ ፡ እለመልማለሁ