Loading
Singer
ፀጋህን ፡ እንጂ ፡ ጽድቄን ፡ አልቆጥር ከሰጠኸኝ ፡ በላይ ፡ ምንም ፡ አልጨምር የማልጠቅም ፡ ባርያ ፡ ታሪክ ፡ የሌለኝ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ እንዳዳነኝ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማንስ ፡ ይከሰኛል አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማን ፡ ይቃወመኛል ሞትና ፡ እርግማን ፡ ተጭኖኝ ፡ ነበር ነፍሴን ፡ አጉብጧት ፡ የሀጥያት ፡ ቀንበር የዓለም ፡ ብርሀን ፡ ኢየሱስ ፡ ሲመጣ ጨለማዬ ፡ ተወገደ ፡ ለእኔም ፡ ብርሀን ፡ ወጣ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማንስ ፡ ይከሰኛል አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማን ፡ ይቃወመኛል አድራሻ ፡ የለኝ ፡ መነሻ ፡ ስፍራ ሥሜ ፡ አይታወቅ ፡ ዘሬ ፡ አይጠራ እንዳላሰብኩት ፡ በውን ፡ በህልሜ ከነአብርሀም ፡ ከነዳዊት ፡ ተመዝግቧል ፡ ሥሜ አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማንስ ፡ ይከሰኛል አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማን ፡ ይቃወመኛል ብርሀኔና ፡ መድኃኒቴ ፡ ነው ታዲያ ፡ እሱን ፡ አልፎ ፡ ሚነካኝ ፡ ማነው ማንስ ፡ ቢመጣ ፡ ምን ፡ ያደርገኛል የጸና ፡ ግንብ ፡ የእሳት ፡ አጥር ፡ ኢየሱስ ፡ ሆኖኛል አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማንስ ፡ ይከሰኛል አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማን ፡ ይቃወመኛል ከተደረገው ፡ ከሆነው ፡ ነገር ጥቂቱም ፡ አይገባኝም ፡ ነበር ሞልቶ ፡ እስከሚፈስ ፡ አየሁ ፡ ምህረቱን ሁሉ ፡ ከእርሱ ፡ ሁሉ ፡ በእርሱ ፡ ለእርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁን አዝ፦ አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማንስ ፡ ይከሰኛል አንድ ፡ ነገር ፡ ግን ፡ አውቃለው ፡ ኢየሱስ ፡ ወዶኛል (፫x) ማን ፡ ይቃወመኛል አዝ፦ ሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን ሁሉን ፡ የሚገዛ ፡ ስራው ፡ ታላቅና ፡ ድንቅ ይገባዋል ፡ ለዘለዓለም ፡ እኛ ፡ ልናንስ ፡ እርሱ ፡ ሊልቅ በመንገዱ ፡ ጻድቅ ፡ በፍርዱ ፡ እውነተኛ ለቃሉ ፡ ታማኝ ፡ ነው ፡ ለስሙ ፡ ቀናተኛ አዝ፦ ሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን ከትንሳኤ ፡ በኩር ፡ ከፍጥረት ፡ መጀመሪያ አልፋና ፡ ኦሜጋ ፡ መክፈቻና ፡ መዝጊያ የቤተ ፡ ክርስቲያን ፡ ራስ ፡ ያለና ፡ የሚመጣ የጌቶች ፡ ሁሉ ፡ ጌታ ፡ ኢየሱስ ፡ ክርስቶስ ፡ ነው አዝ፦ ሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን የርስታችን ፡ መያዢያ ፡ ለቤዛም ፡ ቀን ፡ ያተመን ወደ ፡ እውነት ፡ የሚመራን ፡ በመከራም ፡ ሚያቆመን በሀይሉ ፡ የሞላ ፡ ስጦታውን ፡ ያደለን ከሰማይ ፡ የተላከ ፡ መንፈስ ፡ ቅድስ ፡ አለን አዝ፦ ሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን እግዚአብሔር ፡ አብ ፡ ልጁን ፡ ሰጠን ፡ እግዚአብሄር ፡ ወልድ ፡ እራሱን ፡ ሰጠን መንፈስ ፡ ቅዱስ ፡ ቃሉን ፡ ሰጠን ፡ ቃሉም ፡ እኛን ፡ ለወጠ ቸር ፡ አምላክ ፡ ባለጸጋ ፡ ዘወትር ፡ እጁን ፡ የዘረጋ አያልቅበት ፡ ሁሌ ፡ ሙሉ ፡ ሀሌ ፡ ሀሌሉያ ፡ በሉ አዝ፦ ሀሌሉ ፡ ሀሌሉያ (፬x) ክብር ፡ ለእግዚአብሔር ፡ ይሁን አዝ፦ አንድ ፡ ሰው ፡ ነካኝ ፡ በድንገት ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ነካኝ እስራት ፡ ነበረኝ ፡ ፈታኝ ፡ ድካም ፡ ነበረኝ ፡ አነቃኝ ጥማት ፡ ነበረኝ ፡ አረካኝ ፡ አንድ ፡ ሰው ፡ ነካኝ በርጠሚዎስ ፡ እኔነኝ ፡ ዘመድ ፡ የራቀኝ እድሜ ፡ ልኬን ፡ በልመና ፡ አለም ፡ ያወቀኝ የመንገድ ፡ ጉቶ ፡ እንቅፋት ፡ ሁሉም ፡ ሲሰድበኝ እኔም ፡ ወግ ፡ ሊደርሰኝ ፡ ሆነ ፡ አምላክ ፡ ሊያስበኝ የዳዊት ፡ ልጅ ፡ ሆይ ፡ ና ፡ ማረኝ ፡ ብዬ ፡ ብጣራ ኢየሱስ ፡ መጣ ፡ ዳሰሰኝ ፡ አይኔን ፡ አበራ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ እስራት ፡ ነበረኝ ፡ ፈታኝ ፡ ድካም ፡ ነበረኝ ፡ አነቃኝ ጥማት ፡ ነበረኝ ፡ አረካኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ ሽባ ፡ ነበረ ፡ ማይሰራ ፡ እግሬና ፡ እጄ ሰላሳ ፡ ስምንት ፡ አመታት ፡ ተቆራምጄ መላክ ፡ ሲመጣ ፡ ውሀውን ፡ ሲያንቀሳቅሰው ቀድሞ ፡ የደረሰ ፡ ሲፈታ ፡ ሲሄድ ፡ ስንት ፡ ሰው በድሌ ፡ ሳዝን ፡ በሰው ፡ ዘንድ ፡ እንደተረሳው ኢየሱስ ፡ መጣ ፡ አስነሳኝ ፡ እኔም ፡ ተነሳው አዝ፦ ኢየሱስ ፡ ነካኝ ፡ በድንገት ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ እስራት ፡ ነበረኝ ፡ ፈታኝ ፡ ድካም ፡ ነበረኝ ፡ አነቃኝ ጥማት ፡ ነበረኝ ፡ አረካኝ ፡ ኢየሱስ ፡ ነካኝ ለአስራ ፡ ሁለት ፡ አመታት ፡ እንባ ፡ እንደ ፡ ጅረት ባለ ፡ መድሃኒት ፡ አልቀረኝ ፡ ስንት ፡ ሀገር ፡ ዙረት ትርምስ ፡ አየሁ ፡ በድንገት ፡ ሳልፍ ፡ በመንገዱ በብዙ ፡ ሺዎች ፡ መካከል ፡ ተከቧል ፡ አንዱ ጌታ ፡ መሆኑን ፡ አውቄ ፡ ልብሱን ፡ ብነካ መከራዬ ፡ በድንገት ፡ ምንጩ ፡ ተዘጋ