Loading
Singer
አዝ፦ አንድ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ብቻ ፡ ያለው ሰማይ ፡ ምድርን ፡ የፈጠረው ብቻውን ፡ እውነተኛ ፡ የሆነው ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ የለም አለም ፡ ቢባል ፡ ልክ ፡ አይደለም እውነት ፡ ሆኖ ፡ ላለው ደግሞም ፡ ለነበረው ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x) በሶስትነት ፡ አንድ ፡ ሆኖ ፡ የሚኖር ፡ ስላሴ ክብር ፡ ይገባዋል ፡ የሕዝቡ ፡ ውዳሴ አምላክ ፡ ለሆነው ፡ አምልኮ ፡ ይድረሰው (፪x) አዝ፦ አንድ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ብቻ ፡ ያለው ሰማይ ፡ ምድርን ፡ የፈጠረው ብቻውን ፡ እውነተኛ ፡ የሆነው ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ የለም አለም ፡ ቢባል ፡ ልክ ፡ አይደለም እውነት ፡ ሆኖ ፡ ላለው ደግሞም ፡ ለነበረው ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x) ሁሉ ፡ ከእርሱ ፡ የተገኘ ፡ የፍጥረታት ፡ ምንጭ ያለ ፡ የነበረ ፡ ደግሞም ፡ የሚኖር እርሱ ፡ አንድ ፡ ነው ፡ ሚመስል ፡ የሌለው (፪x) አዝ፦ አንድ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ብቻ ፡ ያለው ሰማይ ፡ ምድርን ፡ የፈጠረው ብቻውን ፡ እውነተኛ ፡ የሆነው ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ የለም አለም ፡ ቢባል ፡ ልክ ፡ አይደለም እውነት ፡ ሆኖ ፡ ላለው ደግሞም ፡ ለነበረው ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x) የአማልክት ፡ አምላክ ፡ ከሁሉ ፡ የበላይ መግደል ፡ ማኖር ፡ ሚችል ፡ ስልጣን ፡ በእጁ ፡ ላይ እውነተኛ ፡ የሆነው ፡ እርሱ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው (፪x) አዝ፦ አንድ ፡ አምላክ ፡ ነው ፡ ብቻ ፡ ያለው ሰማይ ፡ ምድርን ፡ የፈጠረው ብቻውን ፡ እውነተኛ ፡ የሆነው ከእርሱ ፡ በቀር ፡ ሌላ ፡ የለም አለም ፡ ቢባል ፡ ልክ ፡ አይደለም እውነት ፡ ሆኖ ፡ ላለው ደግሞም ፡ ለነበረው ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን (፪x) ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን ክብር ፡ ይሁን (፪x) ፡ ክብር ፡ ይሁን ፡ አሜን