Loading
Singer
ሕዝቡን ፡ ከኃጢአት ፡ ሚያድን ፡ ሚፈውስ ድንቅ ፡ መካር ፡ ኃያል ፡ ስሙም ፡ ኢየሱስ የእስራኤል ፡ መሪ ፡ ታላቁ ፡ መስፍን በቤተልሄም ፡ ተወለደልን (፪x) አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ አሜን ሰባሰገል ፡ መጡ ፡ ከነበሩበት ለተወለደው ፡ ህጻን ፡ ሊሰግዱለት የአዲስ ፡ ኪዳን ፡ በግ ፡ ታላቁ ፡ ጌታ ከላይ ፡ ወረደ ፡ ሕዝቡን ፡ ሊፈታ ሊሆን ፡ ደስታ አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ አሜን ዝማሬ ፡ በመላእክት ፡ አስተጋባ እጣንና ፡ ከርቤም ፡ በበረት ፡ ገባ በምድር ፡ ቅጥርም ፡ ውስጥ ፡ ጽድቅም ፡ ይሆናል እግዚአብሔር ፡ ዓለሙን ፡ እንዲሁ ፡ ወዷል (፪x) አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ አሜን ታናሽ ፡ ከተማ ፡ ቤተልሔም ፡ ሆይ መድሃኒት ፡ ከአንቺ ፡ ወጥቶ ፡ የለም ፡ ወይ ክብር ፡ ምሥጋና ፡ ውዳሴ ፡ ስግደት ለህጻኑ ፡ ኢየሱስ ፡ እናቅርብለት (፪x) አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ አሜን ኮኮብ ፡ ይወጣል ፡ በትር ፡ ይነሳል ለእስራኤል ፡ መዳን ፡ ይሆንለታል ተብሎ ፡ ተነግሮ ፡ ነበር ፡ አሁን ፡ ግን ፡ ሆኗል አምላክ ፡ ከሕዝቡ ፡ ጋራ ፡ ሊታረቅ ፡ ወዷል (፪x) አዝ፦ አንቺ ፡ ቤተልሔም ፡ የይሁዳ ፡ ከተማ ለዓለም ፡ የምሥራች ፡ ከአንቺ ፡ ዘንድ ፡ ተሰማ አሜን