Loading
Singer
አዝ:- አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x) ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x) አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x) ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x) ጨለማው ፡ እጅግ ፡ በርትቶ ተስፋ ፡ የሚጣልበት ፡ ጠፍቶ ግራ ፡ ቀኝ ፡ በሩ ፡ ሲዘጋ ተጣራሁ ፡ ረዳት ፡ ፍለጋ ጩኸቴን ፡ ሰምተህ ፡ ከሰማይ ወርደሃል ፡ በጠላቴ ፡ ላይ ወጀቡን ፡ ጸጥ ፡ አረክልኝ ኢየሱስ ፡ ጋሻ ፡ ሆንክልኝ (፪x) አዝ:- አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x) ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x) ኢየሱስ ፡ የነፍሴ ፡ መድሃኒት ኢየሱስ ፡ ድንቅ ፡ የሰራኅልኝ ኢየሱስ ፡ ተራራውን ፡ ንደህ ኢየሱስ ፡ ሜዳ ፡ አደረክልኝ ኧረ ፡ አይቻልም ፡ ከእንግዲህስ ፡ አልልም በዐይኔ ፡ አይቻለሁ ፡ አልጠራጠርም አንተ ፡ ይሁን ፡ ካልክ ፡ የማይሆን ፡ ይሆናል ወደደም ፡ ጠላም ፡ ፍጥረት ፡ ይሰማሃል ጌታ ፡ ነህ (፪x) ፡ ማን ፡ ይቃወምሃል ባሕሩን ፡ ስትከፍለው ፡ ዐይኖች ፡ አይተውሃል ጌታ ፡ ነህ (፪x) ፡ ኢየሱስ ፡ ማን ፡ ይቃወምሃል ባሕሩን ፡ ስትከፍለው ፡ ዐይኖች ፡ አይተውሃል አዝ:- አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x) ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x) አምንሃለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሃለሁ (፪x) ጭር ፡ ባለው ፡ ደረቅ ፡ ምድረ ፡ በዳ ፡ ውኃ ፡ አፍልቀህልኝ ፡ ጠጥቻለሁ (፪x)