Loading
Singer
ምነው ፡ ሰማያትን ፡ ቀደህ ፡ ብትወርድልኝ ብዬ ፡ እኔ ፡ ስጣራ ፡ ታየኛለህ (፪x) ለካስ ፡ ታየኛለህ ፡ ከሰማያት ፡ በላይ ለእኔ ፡ የምትራራ ፡ ታየኛለህ (፪x) ያልተጠባበኩት ፡ የክብርህን ፡ ስራ ገልጸህ ፡ ልታሳየኝ ፡ ታየኛለህ (፪x) አሁን ፡ ተረዳሁት ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው የአንተ ፡ አላማ ፡ ገባኝ ፡ ታየኛለህ (፪x) ታየኛለህ ፡ ስጠራህ ፡ ትሰማኛለህ ታየኛለህ ፡ የልቤን ፡ ታደምጠኛለህ ታየኛለህ ፡ የደምህ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ ታየኛለህ ፡ ላትጥለኝ ፡ ስለያዝከኝ ኢየሱስ (፪x) (ኢየሱሴ) ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋሴ (ለእኔ ፡ ዋሴ) ፍቅርህን ፡ አስባለሁ (ፍቅርህን ፡ አስባለሁ) ፡ ዘለዓለም ፡ እወድሃለሁ (ዘለዓለም ፡ ወድሃለሁ) (፪x) አምንሃለሁ ፡ አትጥልም ፡ አንተ ፡ አትጐዳም አምንሃለሁ ፡ ጀርባ ፡ አትሰጥም ፡ ደርሰህ ፡ እንደባዳ አምንሃለሁ ፡ መጠጋት ፡ ማቀፍ ፡ ባሕሪህ አምንሃለሁ ፡ ተመካሁ ፡ በማይጥል ፡ ፍቅርህ (፪x) ኢየሱስ (፪x) (ኢየሱሴ) ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ለእኔ ፡ ዋሴ (ለእኔ ፡ ዋሴ) ፍቅርህን ፡ አስባለሁ (ፍቅርህን ፡ አስባለሁ) ፡ ዘለዓለም ፡ እወድሃለሁ (ዘለዓለም ፡ ወድሃለሁ) (፪x) አምንሃለሁ ፡ ታማኝ ፡ ነህ ፡ ከምንም ፡ በላይ አምንሃለሁ ፡ ቃል ፡ ሳይሆን ፡ የልብን ፡ የምታይ አምንሃለሁ ፡ እንደሰው ፡ አይተህ ፡ አተፈርድም አምንሃለሁ ፡ መንገድ ፡ ላይ ፡ ጥለህ ፡ አትሄድም (፪x) ምነው ፡ ሰማያትን ፡ ቀደህ ፡ ብትወርድልኝ ፡ ብዬ ፡ እኔ ፡ ስጣራ ፡ ታየኛለህ (፪x) ለካስ ፡ ታየኛለህ ፡ ከሰማያት ፡ በላይ ለእኔ ፡ የምትራራ ፡ ታየኛለህ (፪x) ያልተጠባበኩት ፡ የክብርህን ፡ ስራ ገልጸህ ፡ ልታሳየኝ ፡ ታየኛለህ (፪x) አሁን ፡ ተረዳሁት ፡ ሁሉ ፡ ለበጐ ፡ ነው የአንተ ፡ አላማ ፡ ገባኝ ፡ ታየኛለህ (፪x) ታየኛለህ ፡ ስጠራህ ፡ ትሰማኛለህ ታየኛለህ ፡ የልቤን ፡ ታደምጠኛለህ ታየኛለህ ፡ የደምህ ፡ ኪዳን ፡ አለኝ ታየኛለህ ፡ ላትጥለኝ ፡ ስለያዝከኝ