Loading
Singer
ለእምባዬ ፡ ዋጋ ፡ ያጣሁ ጸሎቴን ፡ ያልሰማህ ሲመስለኝ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ አምንሃለሁ በችግሬ ፡ አንተን ፡ እንድትረዳኝ አዝ፦ አምንሃለሁ ፡ አምንሃለሁ የተናገርከው ፡ እንደሚሆን በክብር፡ ከላይ ፡ ስትመጣ ስለጣን ፡ ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ እንዲሆን ክንዴ ፡ ላልቶ ፡ ረዳት ፡ ሽቶ ወደታችም ፡ ማቆልቆል ፡ ስጀምር ረድተኸኛል ፡ በመንፈስህ ጉዞዬንም ፡ በተስፋ ፡ እንድቀጥል መድሃኒቴ ፡ መድሃኒቴ ልጠለልህ፡ መከራን እስክሸሽ በአንተ ፡ ሕይወት ፡ እንድጸና እንድቆም ፡ የዓለም ፡ ጊዜ ፡ እስኪመሽ በእምነት ፡ ሳይህ ፡ ስትጣራ ፡ ደም ፡ እያዘነበ ፡ ከጐንህ እያነባው ፡ እመጣለው ፡ ይሰማኛልና ፡ ስቃይህ ተቀበለኝ ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ በሌላ ልድን አልሞክርም የሚያዝንልኝ ፡ የሚወደኝ ፡ እንደአንተ ፡ ያለ ፡ ከቶ ፡ አላገኝም ከመስቀል ፡ በስተኋላ ፡ የሚኖረውን ፡ ታላቅ ፡ ፍዳ ለመቀበል ፡ መርጫለሁ ፡ ከመጠበቅ የሞትን ፡ እዳ ይሁንልኝ ፡ ይህ ፡ ፈቃድህ ፡ ጸሎቴም ፡ በፊትህ ፡ ትሰማ ከአንተ ፡ ፍፁም ፡ እንደልለይ ፡ የሕይወት ፡ ጠዋት ፡ እስክትጠባ