Loading
Singer
አዝ፦ አምንሀለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሀለሁ አምንሀለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሀለሁ (፪x) ሠማይ ፡ ምድር ፡ ያልፍል ፡ ቃሌ ፡ ግን ፡ አያልፍም ከአፌ ፡ የወጣዉ ፡ ቃል ፡ እንዲሁ ፡ አይመለስም ብለህ ፡ እንደተናገርህ ፡ ቃልህን ፡ ፈጸምከዉ ኮራሁብህ ፡ ኢየሱስ፡ አንተ ፡ በሰራኸዉ ብታደርግ ፡ ልክ ፡ ብታፈርስ ፡ ልክ የማትሣሣት ፡ ፍፁም ፡ የሆንክ አንተ ፡ ሥራ ፡ እንጂ ፡ ቃልህን ፡ ላክና ሚከለክልህ ፡ የቱ ፡ ነው ፡ ጀግና ፡ ከአንተ ፡ ወዲያ ፡ ጀግና አዝ፦ አምንሀለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሀለሁ አምንሀለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሀለሁ (፪x) ሁኔታ ፡ ሚሰብከኝ ፡ ሚያስፈራ ፡ ነገር ፡ ነው የሚታየው ፡ ሁሉ ፡ እጅግ ፡ አስደንጋጭ ፡ ነው ቃልህ ፡ ትዝ ፡ ሲለኝ ፡ አይዞህ ፡ ነው ፡ የሚለኝ እንዳልፈራ ፡ እንዳልዝል ፡ ነው ፡ የሚያስታውስኝ መች ፡ በሰው ፡ ስሌት ፡ በአዋቂ ፡ መላ ሆኖ ፡ ያውቅና ፡ የአንተ ፡ እኮ ፡ ሌላ ዛሬ ፡ ርሃብ ፡ ሆኖ ፡ ነገ ፡ ጥጋብ ፡ ነው ሥትል ፡ አምናለሁ ፡ ሁሉ ፡ የአንተ ፡ ነው ሁሉ ፡ በእጅህ ፡ ነው አዝ፦ አምንሀለሁ ፡ ጌታ ፡ አምንሀለሁ አምንሀለሁ ፡ ኢየሱስ ፡ አምንሀለሁ (፪x) ውጣ ፡ ያልከኝ ፡ አንተ ፡ እንሆ ፡ ምድሪቷ ሥሜን ፡ አውጅባት ፡ በርዝመት ፡ ስፋቱዋ አብሬህ ፡ እሆናለሁ ፡ እስከ ፡ መጨረሻው ሥትል ፡ ተቀበልኩኽ ፡ ካሳብህ ፡ ተስማማሁ እንደ ፡ አባቶቼ ፡ በአንተ ፡ ታምኜ እራሴን ፡ ክጄ ፡ በዓለም ፡ ጨክኜ ከኖሩስ ፡ አይቀር ፡ እንዲህ ፡ ነው ፡ ኑሮ አንተን ፡ አክብሮ ፡ ደሞ ፡ አስከብሮ (፪x) ዛሬም ፡ ተመለክ ፡ አንተ ፡ አምላክ ፡ ነህ ዛሬም ፡ ተደነቅ ፡ አንተ ፡ ድንቅ ፡ ንህ ዛሬም ፡ ተወደስ ፡ አንተ ፡ ጀግና ፡ ነህ ዛሬም ፡ ተሞገስ ፡ አንተ ፡ ልዩ ፡ ነህ ሲያንሥህ ፡ ነው ፡ ጭብጨባ (፬x) ሲያንሥህ ፡ ነው ፡ ዕልልታ (፬x)