Loading
Singer
ፀጋህ ፡ ለእኔ ፡ በዝቶ ፡ እዚህ ፡ ደርሻለሁ አንተ ፡ ከቆምክልኝ ፡ ሌላ ፡ ምን ፡ እሻለሁ የገፋኝ ፡ ተገፍቶ ፡ የወጋኝ ፡ ተወጋ ያልያዝኩትን ፡ ልያዝ ፡ እጆቼን ፡ ልዘርጋ ባለሁበት ፡ አልሂድ ፡ ጊዜ ፡ አይለፍብኝ እስቲ ፡ ከመንፈስህ ፡ እፍ ፡ በልብኝ አዝ፦ አምንሀለው ፡ ጌታ ፡ አምንሀለው ቃልህን ፡ ስታከብር ፡ አይቻለው አምንሀለው ፡ ጌታ ፡ አምንሀለው ከግብጽ ፡ ወጥቼ ፡ ምድረበዳ ፡ ዘለኩ ባህር ፡ ተሻግሬ ፡ ዮርዳኖስን ፡ አለፍኩ እያሪኮ ፡ በራፍ ፡ ቆሜ ፡ ለምን ፡ ላልቅስ የትላንቱን ፡ ጌታ ፡ ልታመን ፡ ይልቅስ የግብጽን ፡ ሰራዊት ፡ ባህር ፡ ያሰጠመ እግዚአብሄር ፡ ብርቱ ፡ ነው ፡ ዛሬም ፡ አልደከመም አዝ፦ አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው ቃልኪዳኑን ፡ ሲያከብር ፡ አይቻለው (፪x) አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው የኤናቄል ፡ ልጆች ፡ ቁመናቸው ፡ ሎጋ ውስጣቸው ፡ ባዶ ፡ ነው ፡ በእምነት ፡ ልጠጋ በእነርሱ ፡ አይን ፡ ስታይ ፡ አንበጣ ፡ መስላለው በውስጤ ፡ ያለው ፡ ግን ፡ ኃያል ፡ እግዚአብሔር ፡ ነው እስከመቼ ፡ ድረስ ፡ ፈርቼ ፡ ልኑር ተሻግሬ ፡ ልውረስ ፡ የተስፋይቱን ፡ ምድር አዝ፦ አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው ቃልኪዳኑን ፡ ሲያከብር ፡ አይቻለው (፪x) አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው እምነት ፡ ከመስማት ፡ ነው ፡ መስማትም ፡ በቃሉ ለሚመረምሩት ፡ መልስ ፡ አለው ፡ ለሁሉ ቃሉን ፡ እያነበብኩ ፡ ተስፋውን ፡ ባላምን ጊዜ ፡ ማጥፋት ፡ እንጂ ፡ መመላለስ ፡ ለምን በአባቶቼ ፡ ዘመን ፡ ድንቅን ፡ ያደረገው የጠራኝ ፡ እግዚአብሄር ፡ የጌቶች ፡ ጌታ ፡ ነው አዝ፦ አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው ቃልኪዳኑን ፡ ሲያከብር ፡ አይቻለው (፪x) አምነዋለው ፡ ጌታን ፡ አምነዋለው ከስሞች ፡ በላይ ፡ ስሙ ፡ ሀያል ፡ በሰማይ ፡ በምድር ፡ ሁሉን ፡ ያያል የተዋረደን ፡ ከፍ ፡ ያደርጋል ፡ ታናናሾችን ፡ ያሳድጋል ሁሉ ፡ በእጁ ፡ ነው ፡ በችሎታው ፡ ከልካይ ፡ የለውም ፡ የሚገታው ምስጋና ፡ ክብር ፡ ሞገስ ፡ ለርሱ ፡ ለዘለዓለም ፡ ለንጉሱ አዝ፦ መውደቅ ፡ ለጠላቴ ፡ መዋረድ ፡ ለሰይጣን መድከም ፡ ለስጋዬ ፡ መሸነፍ ፡ ለዓለም ክብር ፡ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም በሰማይ ፡ ይሁን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ አቻ ፡ የለውም ፡ እሱን ፡ መሳይ እርሱ ፡ ብቻውን ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ታናሽም ፡ ታላቅ ፡ የሌለው ስጋ ፡ በፊቱ ፡ ይዋረድ ፡ ዲያቢሎስ ፡ አይቶ ፡ ይንደድ ዓለም ፡ በሞላ ፡ ትስገድ ፡ ለርሱ ፡ ክብር ፡ ይሁንለት ፡ ለንጉሱ አዝ፦ መውደቅ ፡ ለጠላቴ ፡ መዋረድ ፡ ለሰይጣን መድከም ፡ ለስጋዬ ፡ መሸነፍ ፡ ለዓለም ክብር ፡ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም አሶር ፡ ቢነሳ ፡ በበትሩ ፡ እነ ፡ ሰናኬ ፡ ቢፎክሩ ናቡከደነጾር ፡ ቢኮራ ፡ አንበሳው ፡ ፈርኦን ፡ ቢያጓራ ሁሉም ፡ እንደጥላ ፡ አለፉ ፡ ከእግሩ ፡ በታች ፡ ተደፉ እያሸነፈ ፡ እየረታ ፡ አለ ፡ ይኖራል ፡ የኛ ፡ ጌታ ፡ አዝ፦ መውደቅ ፡ ለጠላቴ ፡ መዋረድ ፡ ለሰይጣን መድከም ፡ ለስጋዬ ፡ መሸነፍ ፡ ለዓለም ክብር ፡ ግን ፡ ለኢየሱስ ፡ ይሁን ፡ ለዘለዓለም ጌታ ፡ ከፍይበል ፡ እኛ ፡ ዝቅ ፡ ሊገን ፡ ሊከብር ፡ ሊልቅ እርሱ ፡ ይውረሰው ፡ ሁሉን ፡ ቦታ ፡ በሁሉም ፡ ነገር ፡ ይሁን ፡ ጌታ ይዘምርለት ፡ አፋችን ፡ ያጨብጭብለት ፡ እጃችን ዕልልታው ፡ ይድመቅ ፡ በሆታ ፡ ይህም ፡ ያንሰዋል ፡ ለጌታ