Loading
Singer
አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ፡ ዘወተር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x) በጠዋት ፡ በማታ ፡ በቀን ፡ በሌሊት ምሥጋናዬ ፡ ይድረስ ፡ ዘወትር ፡ በእርሱ ፡ ፊት የአንደበቴን ፡ ፍሬ ፡ ከቶ ፡ አልቆጥብም ብዙ ፡ አድርጐልኛል ፡ አሃሃ ፡ ችዬ ፡ ዝም ፡ አልልም አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x) የሕይወቴ ፡ ጋሻ ፡ ተገን ፡ ሆኖልኛል ስወጣም ፡ ሰገባም ፡ እረፍቱ ፡ ከቦኛል እርሱን ፡ ለማመስገን ፡ በገናዬን ፡ ላንሳ ያደረገልኝን ፡ በፍፁም ፡ ሳልረሳ አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x) ስላደረገልኝ ፡ እጅግ ፡ ብዙ ፡ ውለታ አመልከዋለሁኝ ፡ ሳልሰለች ፡ ለአንድ ፡ አፍታ ከዚህ ፡ ሌላ ፡ ምለው ፡ ምሰጠው ፡ የለኝም ዘምርለታለሁ ፡ እኔስ ፡ እስከ ፡ ዘለዓለም አዝ፦ አምላኬን ፡ ሁልጊዜ ፡ አባርከዋለሁ ምሥጋናው ፡ ዘወትር ፡ ዘወትር ፡ በአፌ ፡ ነው (፪x) አቻምናን ፡ ማለፌ ፡ ሲደንቀኝ አምናን ፡ በምህረትህ ፡ አለፍኩኝ ለዘንድሮም ፡ ቢሆን ፡ አልፈራም ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልሰጋም (፫x) ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልሰጋም (፫x) ጌታ ፡ ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነህ ፡ አልሰጋም እጅግ ፡ ብዙ ፡ ውለታ ፡ ለነፍሴ አድርገህላታል ፡ ኢየሱሴ (፪x) አሳቤን ፡ ጭንቀቴን ፡ ወስደሃል አምላኬ ፡ አሳርፈኸኛል በሕይወቴ ፡ ልትኖር ፡ መርጠሃል የእኔንም ፡ ምሥጋና ፡ ወድሃል (፪x) የእኔንም ፡ ምሥጋና ፡ ወደሃል ፡ መርጠሃል ፡ መርጠሃል የእኔንም ፡ አምልኮ ፡ መርጠሃል እጅግ ፡ ብዙ ፡ ውለታ ፡ ለነፍሴ አድርገህላታል ፡ ኢየሱሴ (፮x)