Loading
Singer
አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ ገና ፡ ሌሊት ፡ ሳለ ፡ ከእንቅልፌ ፡ እነሳለሁ የፊትህን ፡ ብርሃን ፡ ላይ ፡ እፈልጋለሁ ነፍሴ ፡ እንደ ፡ ውኃ ፡ አንተን ፡ ትጠማለች በቀንም ፡ በማታም ፡ ትናፍቅሃለች አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ እጆቼን ፡ በሥምህ ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እያነሳሁ በዘወትር ፡ ፀሎት ፡ ምሥጋና ፡ አቀርባለሁ በሁለንተናዬም ፡ እገዛልሃለሁ ምንጊዜም ፡ የአንተው ፡ ነኝ ፡ በቤትህ ፡ እኖራለሁ አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ ሺህ ፡ ዓመት ፡ በሥጋ ፡ ከመኖር ፡ በከንቱ እውነትህን ፡ አውቆ ፡ ይሻላል ፡ መሞቱ መስቀልህን ፡ መያዝ ፡ መርጫለሁ ፡ እኔ ይህ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ የነፍሴ ፡ ውሳኔ አዝ፦ አምላኬ (፪x) ፡ ወደ ፡ አንተ ፡ እገሰግሳለሁ ኃይልህን ፡ ክብርህን ፡ እንዳይ ፡ እሮጣለሁ ፊትህን ፡ አሳየኝ ፡ ደስታን ፡ እጠግባለሁ ምህረትህ ፡ ይብዛልኝ ፡ በሕይወት ፡ እኖራለሁ