Loading
Singer
አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፪x) ከቤት ፡ ከመንደሩ ፡ ከአባቱ ፡ ቤት ፡ ወጣ ዘሩን ፡ እንደ ፡ አሸዋ ፡ ሊያበዛለት ፡ መጣ የብዙ ፡ ህዝብ ፡ አባት ፡ በኩር ፡ አደረገው መሃኑን ፡ አብረሃም ፡ በልጅ ፡ ልጅ ፡ ባረከው (፫x) አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x) የገዛ ፡ ወንድሞቹ ፡ ለባዕድ ፡ ሰዎች ፡ ሸጡት በህልሙ ፡ አንዳች ፡ እንዳይሆን ፡ አሳልፈው ፡ ሰጡት ነገ ፡ ነገን ፡ ወልዶ ፡ እውነቱ ፡ ወጣና ወድቀው ፡ ሰገዱለት ፡ ዮሴፍ ፡ ተሾመና (፫x) አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x) የበግ ፡ ጅራት ፡ ሲከተል ፡ ግራገሩ ፡ እረኛ ንግሥናውን ፡ አያውቅ ፡ መሆኑን ፡ ተረኛ ውጣ ፡ ውረዱን ፡ አልፎ ፡ በትሩን ፡ በእጁ ፡ ሰጠው እልፍ ፡ ገዳይ ፡ አምላክ ፡ ዙፋን ፡ ላይ ፡ አስቀመጠው (፫x) አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x) አናብስቶች ፡ ጉድጓድ ፡ ውስጥ ፡ ጣሉት ፡ ቀንተውበት ከፀሎት ፡ ሌላ ፡ ምክኒያት ፡ ሰበብ ፡ አጥተውበት አልፈቀደላቸውም ፡ እንዲቀለጣጥሙት የዳንኤልን ፡ አምላክ ፡ ተባለ ፡ አምልኩት (፫x) አዝ፦ አምላኬ ፡ እንዲህና ፡ እንዲያ ፡ ያደርጋል ፡ ላረፉበትማ ምንኛ ፡ ያስደስታል ፡ በማዳን ፡ ስልቱማ ማንም ፡ አይደርስበት ፡ ሲረዳና ፡ ሲያነሳ አቤት ፡ ሲችል ፡ ሲያውቅበት (፫x)