Loading
Singer
አዝ፦ አምላኬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x) ጌታዬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x) በፊቱ ፡ እጣንን ፡ ከማጠን ፡ በቀር አምልኮ ፡ ስግደትን ፡ ከማቅረብ ፡ በቀር ምሥጋናን ፡ ዝማሬን ፡ ከመስጠት ፡ በቀር ያለኝን ፡ በፊቱ ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር ሌላ ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ሌላ (፬x) ሠማይ ፡ ከሠማያት ፡ በላይ ከፍ ፡ ብሎ ፡ ቢኖር ፡ ሌላ ፡ ሠማይ ጌታዬን ፡ ሊይዘው ፡ አይችልም ነውና ፡ ከሁሉም ፡ የበላይ (፪x) የለውም ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ የለውም ፡ የበላይ እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ ጌታዬ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የበላይ አዝ፦ አምላኬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x) ጌታዬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x) በፊቱ ፡ እጣንን ፡ ከማጠን ፡ በቀር አምልኮ ፡ ስግደትን ፡ ከማቅረብ ፡ በቀር ምሥጋናን ፡ ዝማሬን ፡ ከመስጠት ፡ በቀር ያለኝን ፡ በፊቱ ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር ሌላ ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ሌላ (፬x) አየሁኝ ፡ የእርሱን ፡ ታላቅነት ተረዳሁ ፡ የብርታቱን ፡ ጉልበት ፅኑ ፡ ነው ፡ የለም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር በሠማይ ፡ ቢሆን ፡ በዚህች ፡ ምድር (፪x) እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ የበላይ (፪x) ጌታዬ ፡ ነው ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ የበላይ አዝ፦ አምላኬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x) ጌታዬ ፡ ከአማልክት ፡ በላይ ታላቅ ፡ ነውና ፡ ሃሃ (፫x) በፊቱ ፡ እጣንን ፡ ከማጠን ፡ በቀር አምልኮ ፡ ስግደትን ፡ ከማቅረብ ፡ በቀር ምሥጋናን ፡ ዝማሬን ፡ ከመስጠት ፡ በቀር ያለኝን ፡ በፊቱ ፡ ከማፍሰስ ፡ በቀር ሌላ ፡ ምን ፡ እሰጥሃለሁ ፡ ሌላ (፬x) በብርቱ ፡ ጉልበቱ ፡ ታመንኩኝ በፅድቅም ፡ ስራው ፡ ተመካሁኝ በክንዱ ፡ ሁሉንም ፡ ያዘዘ የምድርን ፡ ዳርቻ ፡ የያዘ ላድንቀው ፡ ዛሬም ፡ የእኔን ፡ ጌታ ላክብረው ፡ በጣፋጩ ፡ ዜማ ገዥ ፡ ነህ ፡ ሁሉንም ፡ የረታህ እያልኩኝ ፡ የለህም ፡ የበላይ የለህም ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ የለህም ፡ የበላይ (፪x) አንተ ፡ ነህ ፡ የበላይ ፡ የበላይ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ የበላይ (፪x)