Loading
Singer
ሃፍረት ፡ አስቀርቅሮ ፡ አንገቴ ፡ ላይ ፡ ቀና የበደሌ ፡ ቀንበር ፡ በላዬ ፡ ባሰና በቀራንዮ ፡ ላይ ፡ ባፈሰስከው ፡ ደምህ ድፍረት ፡ ሆኖልኛል ፡ እንድቆም ፡ በፊትህ አዝ፦ አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x) ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፪x) ሥምህን ፡ ጠርቼ ፡ ድኛለሁኝና ፡ (አምላኬ) በላይ ፡ በላዩ ፡ ላይ ፡ ልደርብ ፡ ምሥጋና ፡ (አምላኬ) ኧረ ፡ እኔ ፡ አመለጥኩኝ ፡ አንተን ፡ በማመኔ ፡ (አምላኬ) በሰውነቴ ፡ ላይ ፡ ታወቀኝ ፡ መዳኔ ፡ (አምላኬ) ታድያ ፡ እንዴት ፡ ዝም ፡ ይላል ፡ የተደረገለት ፡ (አምላኬ) በድግድግ ፡ ጨለማ ፡ ብርሃን ፡ የሆንክለት ፡ (አምላኬ) አዝ፦ አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x) ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፪x) አንተን ፡ በመምረጤ ፡ አላፈርኩም ፡ ከቶ ሰላም ፡ ሆኖልኛል ፡ ቃልህ ፡ ልቤ ፡ ገብቶ መታመኛዬ ፡ ነህ ፡ ኮርቼብሃለሁ በሕይወቴ ፡ ዘምን ፡ አንተን ፡ አመልካለሁ አዝ፦ አምላኬ ፣ አምላኬ (፫x) ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፪x) ስገጅ ፡ ስገጅ ፡ አለኝ ፡ ተገርፈሃልና ፡ (አምላኬ) ልሰጥ ፡ የሚገባኝ ፡ ይኸው ፡ የእጅ ፡ መንሻ ፡ (አምላኬ) ግሩም ፡ የዕርቅ ፡ ቀን ፡ ስለሆነ ፡ ለእኔ ፡ (አምላኬ) ምሥጋናዬ ፡ ኢኸው ፡ ይፈሳል ፡ ከልቤ ፡ (አምላኬ) ከጻድቃን ፡ ማህበር ፡ እኔም ፡ ልቀላቀል ፡ (አምላኬ) ለዚህ ፡ በቅቻለሁ ፡ ለክብር ፡ ልታሰብ ፡ (አምላኬ) አዝ፦ አምላኬ ፡ (አምላኬ) ፣ አምላኬ ፡ (አምላኬ) (፫x) ክብሬ ፡ ነህ ፡ ማዕረጌ (፫x)