Loading
Singer
አዝ፦ አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ልዩ ፡ ነው በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ማኖር ፡ ልማዱ ፡ ነው (፪x) እስቲ ፡ ልፎካከር ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ በምስራቅ ፡ በምዕራብ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x) ትልቅ ፡ ነው ፡ ብዬ ፡ መታሁት ፡ እንጂ ፡ መቼ ፡ ፈራሁት በበረሃ ፡ ውስጥ ፡ አስተምሮኛል ፡ ኑሮ ፡ የእኔ ፡ አባት (፪x) የተደበቀው ፡ ፀጋ ፡ ሲወጣ ፡ ከኮሮጆዬ መውደቁን ፡ አውቆ ፡ ፈርቶ ፡ ሸሽቶኛል ፡ ባለ ፡ ጋራዬ (፪x) አዝ፦ አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ልዩ ፡ ነው በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ማኖር ፡ ልማዱ ፡ ነው (፪x) እስቲ ፡ ልፎካከር ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ በምስራቅ ፡ በምዕራብ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x) የተዘጋው ፡ ከፈተውና ፡ ከፊት ፡ ከፊቴ መሸነፍ ፡ ሳይሆን ፡ ያጋጥመኛል ፡ ድል ፡ በሕይወቴ (፪x) የተዘራውን ፡ በቅሎ ፡ አየሁት ፡ አልጨነገፈም በድርቁ ፡ ወራት ፡ የሌላው ፡ ሲደርቅ ፡ የእኔ ፡ አልደረቀም (፪x) አዝ፦ አምላክ ፡ ያለው ፡ ይምጣ ፡ የእኔ ፡ አምላክ ፡ ልዩ ፡ ነው በምድረ ፡ በዳ ፡ ላይ ፡ ማኖር ፡ ልማዱ ፡ ነው (፪x) እስቲ ፡ ልፎካከር ፡ በሰሜን ፡ በደቡብ በምስራቅ ፡ በምዕራብ ፡ እርሱ ፡ ነው ፡ እግዚአብሔር (፪x) ምን ፡ ልበል ፡ ምን ፡ ላድርግ ፡ ልቤ ፡ መደነቅ ፡ ተሞላ በአንዱ ፡ ስገረም ፡ ሌላው ፡ እዚህ ፡ ደግሞ ተዓምር ፡ ነው ፡ ከማለት ፡ ሌላ ድንቅ ፡ ነው ፡ ከማለት ፡ ሌላ ልዩ ፡ ነው ፡ ከማለት ፡ ሌላ (፪x)