Loading
Singer
የምሥጋናን ፡ መስዋዕት ፡ እሰዋለሁ የከንፈሬን ፡ ፍሬ ፡ አቀርባለሁ እግዚአብሔር ፡ ብቻህን ፡ አምላክ ፡ ነህና ልትወደስ ፡ ይገባሃልና (፪x) ይገባሃል ፡ አሜን ፡ ይገባሃል (፬x) . (1) . ፡ በበገና በአዲስ ፡ ዝማሬ ፡ በምሥጋና እቀኝልሃለሁኝ ፡ በክብሬ ዝማሬም ፡ ይፈልቃል ፡ ከከንፈሬ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ላንተ (፬x) ይገባሃል ፡ አሜን ፡ ይገባሃል (፬x) ያደረጋትን ፡ ድንቅ ፡ ልጸሙ በአደባባዮቹ ፡ የምትቆሙ እስኪ ፡ ተቀኙለት ፡ ለዚህ ፡ ጌታ ከቅዱሳን ፡ ጋራ ፡ በደስታ ክብር ፡ ለአንተ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ላንተ (፬x) ይገባሃል ፡ አሜን ፡ ይገባሃል (፬x) ሠማያትን ፡ በስንዝር ፡ የለካህ (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) የምድርን ፡ መሰረት ፡ ያጸናህ (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) ባሕሩንና ፡ የብሱን ፡ የለየህ (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) የብርታትህን ፡ ጉልበት ፡ ያሳየኸን (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) ሃሌሉያ ፡ ሆ ፡ ሃሌሉያ (፬x) ዙፋንህ ፡ ከጥንት ፡ ከዘለላለም (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) የእኛ ፡ ጌታ ፡ የሚመስለህ ፡ የለም (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) የሁሉ ፡ አዛዥ ፡ የሁሉ ፡ የበላይ (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) እግዚአብሔር ፡ ነህ ፡ ብቻህን ፡ ኤልሻዳይ (ኦ ፡ ሃሌሉያ ፡ ክብር ፡ ሁሉ ፡ ለአንተ ፡ ይሁን) ሃሌሉያ ፡ ሆ ፡ ሃሌሉያ (፬x) ሃሌሉያ ፡ ሆ ፡ ሃሌሉያ (፬x)