Loading
Singer
ያበጃጁኝ ፡ እጆችህ ፡ እንዴት ፡ የተዋቡ ፡ ናቸው የደሙትም ፡ እጆችህ ፡ እኔንም ፡ ያቀፉ ፡ ናቸው ዛሬም ፡ መጥተህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ጫናቸው (፪x) የማይጠገብ ፡ ነው ፡ የአንተ ፡ መገኘት እንደ ፡ ወንዝ ፡ የሚፈስ ፡ አለበት ፡ በእርግጥ (፪x) አዝ፦ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እሰግዳለሁ ላከበርከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እሰግዳለሁ ላከበርከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ አንተ ፡ ከነካኸኝ ፡ ምን ፡ ይቀርብኛል ክብርህ ፡ ይህን ፡ ልቤን ፡ ፈጽሞ ፡ ያጠግባል (፪x) አዝ፦ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ ለወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ለአንተ ፡ እገዛለሁ ለወደድከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ አንተ ፡ ስትጭንብኝ ፡ ሙሉ ፡ ሰው ፡ እሆናለሁ እስራቴ ፡ ሁሉ ፡ ጠፍቶ ፡ አገኛለሁ በነካኸኝ ፡ ጊዜ ፡ ጉልበቶቼ ፡ ጸኑ በረታሁ ፡ በክብርህ ፡ ወጣሁኝ ፡ ዳገቱን አዝ፦ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ፊትህ ፡ እደፋለሁ ለመረጥከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ አሜን ፡ አሜን ፡ አሜን ፡ ብዬ ፡ ፊትህ ፡ እደፋለሁ ለመረጥከኝ ፡ ጌታ ፡ ምን ፡ እላለሁ ያበጃጁኝ ፡ እጆችህ ፡ እንዴት ፡ የተዋቡ ፡ ናቸው የደሙትም ፡ እጆችህ ፡ እኔንም ፡ ያቀፉ ፡ ናቸው ዛሬም ፡ መጥተህ ፡ በእኔ ፡ ላይ ጌታዬ ፡ ሆይ ፡ ጫናቸው (፪x)