Loading
አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ ብቻውን ፡ አምላክ ፡ ነው (፪x) አመልከዋለሁ ፡ የማይጠፋው ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ የወደደኝ ፡ በደሙ ፡ ያጠበኝ ፡ አንድዬ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው ፡ ውድ ፡ ወዳጄ ፡ ነው አመልክሃለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠ ፡ ሌላ ፡ ማነው አመልከዋለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ሌላ ፡ ማነው ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ማነው ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማነው ፡ ማነው የሚታዩትና ፡ የማይታዩትም ፡ ዙፋናትህ (፪x) ጌትነት ፡ ወይም ፡ አለቅነት ፡ ሥልጣናት በሠማይና ፡ በምድር ፡ ያሉት ፡ ፍጥረት ፡ ሁሉ (፪x) በእርሱ ፡ ተፈጥረዋል ፡ ኧረ ፡ እርሱ ፡ ፍጡር ፡ አይደለም በኢየሱስ ፡ ተፈጥረዋል ፡ ወዳጄ ፡ ፍጡር ፡ አይደለም ዲያቢሎስ ፡ የተቀላቀለ ፡ ነገር ፡ ቢሰብክም ክርስትና ፡ መገለጥ ፡ ነው ፡ አልታለልም የእግዚአብሔርን ፡ የክብሩን ፡ እውቀት ፡ ብርሃን በውስጤ ፡ ጨለማን ፡ ያበራ ፡ ጌታ ፡ ይመስገን በእግዚአብሔርና ፡ በሰውም ፡ መካከል ፡ ያለው ፡ መካከለኛው (፪x) አንድ ፡ ነው ፡ እርሱም ፡ ሰው ፡ የሆነው ፡ ክርስቶስ ፡ ነው ነፍሱንም ፡ ለሁሉ ፡ ቤዛ ፡ የሰጠው ፡ የሰጠ መልክተኛ ፡ ብቻ ፡ አይደለም ፡ መዳን/ሕይወት ፡ በእርሱ ፡ ነው (፪x) ብቻም ፡ ብዙ ፡ አማልክትና ፡ ብዙ ፡ ጌቶች ፡ አሉ ጌታዬ ፡ አይደሉም ፡ በውሸት ፡ ዕውቀት ፡ ሰውን ፡ ያታለሉ ሠማይም ፡ ቢሆን ፡ በምድር ፡ ላይ ፡ ከአማልክት ፡ አሉ ኢየሱስ ፡ ብቻ ፡ ነው ፡ አዳኝ ፡ የተቀባ ፡ አዳኝ ፡ እውነቱ ፡ ሲታይ አዝ፦ አመልክሃለሁ ፡ ብቻውን ፡ አምላክ ፡ ነው (፪x) አመልከዋለሁ ፡ የማይጠፋው ፡ የዘመናት ፡ ንጉሥ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ የወደደኝ ፡ በደሙ ፡ ያጠበኝ ፡ አንድዬ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ በማንም ፡ የማለውጠው ፡ ውድ ፡ ወዳጄ ፡ ነው አመልክሃለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ ነፍሱን ፡ የሰጠ ፡ ሌላ ፡ ማነው አመልከዋለሁ ፡ ጌታዬም ፡ አምላኬም ፡ እርሱ ፡ ነው አመልከዋለሁ ፡ ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ሌላ ፡ ማነው ስለእኔ ፡ በመስቀል ፡ የሞተ ፡ ማነው ከአንተ ፡ ሌላ ፡ ማነው ፡ ማነው
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.