Loading
Singer
እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ያደረገልን (፪x) ሳንጠፋ ፡ ቀኑ ፡ ሳይጨልም ፡ ደረሰልን (፪x) እግዚአብሔር ፡ ድንቅ ፡ ነገር ፡ ነው ፡ ያደረገልን (፪x) ሳንጠፋ ፡ ሳይመሽብን ፡ ደረሰልን (፪x) ወጥመዱ ፡ ተሰባበረ ፡ እኛም ፡ አመለጥን (፪x) አመለጥን (፬x) አይቶ ፡ ልቡ ፡ አልችል ፡ ሲለው ፡ አንድያ ፡ ልጁን ፡ ሰደደው (፪x) አይቶ ፡ ልቡ ፡ አልችል ፡ ሲለው ፡ የኔ ፡ ጌታ ፡ አንድያ ፡ ልጁን ፡ ሰደደው (፪x) ወዶ ፡ ስለመረጥኝ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አስቀመጠኝ (፪x) ወዶ ፡ ስለመረጥኝ ፡ ኢየሱሴ ፡ በአብ ፡ ቀኝ ፡ አስቀመጠኝ (፪x) ተናጠቀልኝ ፡ ጠላቴን ፡ ተበቀለልኝ (፪x) ተናጠቀልን ፡ ጠላትን ፡ ተበቀለልን (፪x) አመለጥን (፬x) የእግዚአብሔር ፡ ምሕረቱ ፡ ስፋቱ ፡ ጥልቀቱ (፪x) የጌታዬ ፡ ቸርነቱ ብዛቱ ፡ ጥልቀቱ (፪x) አይደረስበትም (፬x) አንድያ ፡ ሆኖ ፡ ከሰማያት ፡ መጣ በኩር ፡ ሆኖ ፡ ወደሰማይ ፡ ገባ ወንድሞቹን ፡ አስከትሎ ፡ ኋላ አንድያ ፡ ሆኖ ፡ ከአባቱ ፡ እቅፍ ፡ ወጣ በኩር ፡ ሆኖ ፡ ወደአባቱ ፡ ገባ እኛን ፡ እኛን ፡ አስከትሎ ፡ ኋላ ጠላቴ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ ልፋቱ ፡ ከንቱ ፡ ነው እኔ ፡ እንደሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ካመለጥሁ ፡ ቆየሁ ጠላቴ ፡ ከንቱ ፡ ነው ፡ እሩጫው ፡ ከንቱ ፡ ነው እኔ ፡ እንደሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ካመለጥሁ ፡ ቆየሁ እኔ ፡ እንደሁ ፡ በጌታ ፡ ካመለጥኩ ፡ ቆየሁ እኔ ፡ እንደሁ ፡ በኢየሱስ ፡ ካመለጥሁ ፡ ቆየሁ አመለጥቁኝ (፮x)