Loading
Singer
አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x) ጌታን ፡ የማያውቅ ፡ በጨለማ ፡ ይኖራል በምድርም ፡ ሲኖር ፡ ተደናብሮ ፡ ያልፋል የዓለም ፡ ዝብርቅርቅ ፡ ጊዜያዊ ፡ እኮ ፡ ነው የዘለዓለም ፡ ሕይወት ፡ ያለው ፡ በኢየሱስ ፡ ብቻ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x) የፈጠረህማ ፡ እጅጉን ፡ ቢወድህ አንድያ ፡ ልጁን ፡ በነጻ ፡ እንዲሁ ፡ ሰጠህ አንድ ፡ ልጁን ፡ ሰጠህ ምክንያትን ፡ አታብዛ ፡ ሰበብህን ፡ አቁም ይልቅ ፡ ልቦናህን ፡ ወደ ፡ አምላክም ፡ መልስ አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x) ነገ ፡ ዛሬ ፡ አትበል ፡ ነገ ፡ የአንተ ፡ አይደለም የመዳኛ ፡ ሰዓት ፡ ቢኖር ፡ አሁኑኑ ፡ ነው ሰዓቱ ፡ አሁን ፡ ነው አምልጠኸው ፡ ውጣ ፡ ያሰረህ ፡ ጠላት ፡ ነው ትብታብህ ፡ ይፈታል ፡ ኢየሱስን ፡ ጌታህ ፡ ስታደርገው አዝ፦ ኢየሱስ ፡ እውነት ፡ ሕይወት ፡ ነው ኢየሱስ ፡ አማራጭ ፡ የለው በእርሱ ፡ መዳን ፡ በእርሱ ፡ ነው ፡ በሉ (፪x)