Loading
በለጋነት ፡ ልቤ ፡ ፍቅርህ ፡ አሸንፎኛል ከአንተ ፡ የትም ፡ አልሄድም አንተ ፡ ተመችተኸኛል ቃላትም ፡ የማይገልጹት ፡ ሰማያዊ ፡ ደስታ በህይወት ፡ መመስከር ፡ መገዛት ፡ ለጌታ እኔ ፡ ለብቻዬ ፡ ስሆን ፡ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ የአባትነቱን ፡ ፍቅር ፡ ቀምሻለሁ ጌታን ፡ አውቀዋለሁ ጌታን ፡ አመልካለሁ ለጌታ ፡ እገዛለሁ ጌታን ፡ እወደዋለሁ ኢየሱሴ ፡ አንተን ፡ ምን ፡ ብዬ ፡ ልግለጽህ ቃላቶች ፡ አነሱ ፡ በምን ፡ ልተርክህ እስከ ፡ ዛሬ ፡ ማውቀው ፡ የሚደንቅ ፡ ነገር እጅጉን ፡ ትንሽ ፡ ነው ፡ ከአንተ ፡ ሲወዳደር አማኑኤል (አማኑኤል) ፤ አማኑኤል አማኑኤል (ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው) ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው እግዚአብሔር (እግዚአብሔር) አባት ፡ ለልጆቹ ፡ ሃይማኖት ፡ ያወርሳል ልጅ ፡ የተማረውን ፡ ስርዓት ፡ ይፈጽማል ግን ፡ የጌታን ፡ ፍቅር ፡ አላስተዋለውም ሃይማኖቱን ፡ እንጂ ፡ ጌታን ፡ ከቶ ፡ አልተቀበለም ጌታዬ ፡ ግን ፡ ድኅነት ለሚሹህ ፡ ቅርብ ፡ ነህ አንተ ፡ ትሻሃላለህ አንተ ፡ ታዋጣለህ አምላኬ ፡ ሆይ ፡ አንተን ፡ ተረድቼሃለሁ በወረስኩት ፡ ሳይሆን ፡ በግሌ ፡ አውቅሃለሁ ከቤትህ ፡ ርቄ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ ፍቅርህ ፡ ማርኮኛል ፡ አንተን ፡ መርጫለሁ አማኑኤል (አማኑኤል) ፤ አማኑኤል አማኑኤል (ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው) ከእኔ ፡ ጋር ፡ ነው እግዚአብሔር (እግዚአብሔር)
Comments
Comments, source notes, and missing-line fixes from contributors.
Revision history
Approved updates stay visible so the editing trail remains transparent.