Loading
Singer
ድምጹን ፡ እያሰማ ፡ ቀኔን ፡ የሚያበራ ፡ አላውቅም ፡ እንደጌታ መጪውንም ፡ ዘመን ፡ ቀድሞ ፡ የሚናገር ፡ አላየሁም ፡ ከእርሱ ፡ በቀር ለዘመኔ ፡ ባዳ ፡ እንዳልሆን ፡ እንግዳ ፡ ሚስጢሩን ፡ ይገልጸዋል ፡ በጓዳ አምላኬ ፡ ኦ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) አዝ፦ አልወጣም ፡ ከፊትህ (ከፊትህ) ፡ አይለየኝ ፡ መንፈስህ (መንፈስህ) አላማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x) ድምጽህን ፡ ሰምቼ ፡ እረፍት ፡ ተሞልቼ ፡ ኖሬያለሁ ፡ ጸንቼ ከአንተ ፡ ተጠግቼ ፡ ልብህን ፡ አግኝቼ ፡ ቀረሁኝ ፡ ገብቼ ፊትህ ፡ እቆማለሁ ፡ ኃይልህን ፡ አያለሁ አልወጣም ፡ ከክብርህ ፡ ውስጥ ፡ ወስኛለሁ አምላኬ ፡ ሆ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) አዝ፦ አልወጣም ፡ ከፊትህ (ከፊትህ) ፡ አይለየኝ ፡ መንፈስህ (መንፈስህ) አላማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x) እኔስ ፡ አውቄያለሁ ፡ ሚስጥሩን ፡ አግኝቻለሁ ከመንፈስህ ፡ ወዴት ፡ እሄዳለሁ መነሻ ፡ መድረሻም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ብያለሁ ክብርህን ፡ ሳይ ፡ ጌታ ፡ እጠግባለሁ (፪x) አምላኬ ፡ ሆ ፡ እንዴት ፡ እንዴት ፡ ልዩ ፡ ነህ (፪x) አዝ፦ አልወጣም ፡ ከፊትህ (ከፊትህ) ፡ አይለየኝ ፡ መንፈስህ (መንፈስህ) አላማዬ ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ መኖሪያዬ ሕይወት ፡ ትርጉም ፡ ያለው ፡ በአንተ ፡ ነው ፡ ጌታዬ (፪x) አልወጣም ፡ ከፊትህ አልወጣም ፡ ከፊትህ (አልወጣም ፡ ከፊትህ) (፫x) ከማደሪያህ ፡ ከመቅደስህ አልወጣም ፡ ከፊትህ