Loading
Singer
አስገረመኝ/አስደነቀኝ ፡ ነገሬን ፡ ውብ ፡ አረገና አፌን ፡ ሞላው ፡ በአዲስ ፡ ቅኔ ፡ በምሥጋና በዝማሬ ፡ እገባለሁ ፡ ወደ ፡ ቤቱ ሥራዬ ፡ ተሰርቷልና ፡ በምረቱ ኃይሌን ፡ አድሶት ፡ ጌታዬ ፡ ወጥቻለሁ ፡ አሃሃ ፡ ነቅቻለሁ ከዚያ ፡ ላይ ፡ ማን ፡ ያወርደኛል ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ አሃሃ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ጠላቴ ፡ አታገኘኝም ፡ በትላንቱ ፡ በትላንቱ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ አውጥቶኛል ፡ በሰዓቱ ፡ በሰዓቱ በሰዓቱ ፡ በሰዓቱ (፬x) የማታ ፡ ለቅሶዬ ፡ ጠዋት ፡ ተለውጦ እንደ ፡ መርደኪዮስ ፡ ታሪክ ፡ ነገር ፡ ተገልብጦ በኮረብታ ፡ ሆኜ ፡ መዝሙር ፡ ዘምራለሁ ፡ ሆ እኔ ፡ ከላይ ፡ ሆኜ ፡ ጠላቴን ፡ ረግጫለሁ አልወርድም ፡ ከከፍታዬ ፡ ላይ እግዚአብሔር ፡ አርጐኛል ፡ የበላይ ዝቅታው ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ጠላቴ እግዚአብሔር ፡ ጥሎሃል ፡ ከፊቴ እግዚአብሔር ፡ ቀኑን ፡ እስኪሰጥ ፡ ድረስ አይኔ ፡ ዝም ፡ ብሎ ፡ እምባን ፡ ቢያፈስ እንዳለቀስኩኝ ፡ መቼ ፡ ቀረሁኝ የምስቅበት ፡ ዘመን ፡ መጣልኝ አፌን ፡ ምሥጋና ፡ ኦሆ ፡ ይኸው ፡ ሞላኝ (፪x) አልወርድም ፡ ከከፍታዬ ፡ ላይ እግዚአብሔር ፡ አርጐኛል ፡ የበላይ ዝቅታው ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ጠላቴ እግዚአብሔር ፡ ጥሎሃል ፡ ከፊቴ የእግዚአብሔር ፡ ጉልበት ፡ የክንዱ ፡ ብርታት ይህንን ፡ አድርጓል ፡ ሰርቶ ፡ ታምራት ክፉ ፡ በሆኑት ፡ ቀናቶች ፡ ፈንታ ደስታ ፡ አጠገበኝ ፡ ኤልሻዳዩ ፡ ጌታ አመልከዋለሁ ፡ ሁሌ ፡ ጠዋት ፡ ማታ (፪x) ኃይሌን ፡ አድሶት ፡ ጌታዬ ፡ ወጥቻለሁ ፡ አሃሃ ፡ ነቅቻለሁ ከዚያ ፡ ላይ ፡ ማን ፡ ያወርደኛል ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ፡ አሃሃ ፡ ከፍ ፡ ብያለሁ ጠላቴ ፡ አታገኘኝም ፡ በትላንቱ ፡ ኦሆሆ ፡ በትላንቱ ኢየሱስ ፡ መጥቶ ፡ አውጥቶኛል ፡ በሰዓቱ ፡ ኦሆሆ ፡ በሰዓቱ በሰዓቱ ፡ በሰዓቱ (፬x) ልቤን ፡ አልጥልም ፡ ከጠፉት ፡ አህዮች ፡ ላይ እግዚአብሔር ፡ መጥቷል ፡ ሊሰጠኝ ፡ ከዚያ ፡ በላይ ሃሳቡ ፡ ለእኔ ፡ ምንጊዜም ፡ የመልካም ፡ ነው ታምር ፡ ሲሰራ ፡ በሕይወቴ ፡ አይቻለሁ አልወርድም ፡ ከከፍታዬ ፡ ላይ እግዚአብሔር ፡ አርጐኛል ፡ የበላይ ዝቅታው ፡ ያንተ ፡ ነው ፡ ጠላቴ እግዚአብሔር ፡ ጥሎሃል ፡ ከፊቴ