Loading
Singer
"በሕይወትህ ፡ ዕድሜ ፡ ሁሉ ፡ ማንም ፡ አይቋቋምህም ከሙሴ ፡ ጋር ፡ እንደሆንኩ ፡ እንዲሁ ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እሆናለሁ አልጥልህም ፡ አልተውህም ፣ አልጥልህም ፡ አልተውህም" ከሙሴ ፡ ጋር ፡ እንደነበርኩ ፡ ከአንተ ፡ ጋርም ፡ እሆናለሁ ብቻ ፡ በርታ ፡ ጽና ፡ ልጄ ፡ ሁሉን ፡ መልካም ፡ አደርጋለሁ ምንም ፡ ነገር ፡ ዓይነካህም ፡ እርግማን ፡ አይደርስብህም በጠላት ፡ ላይ ፡ ትጫማለህ ፡ ዘንዶ ፡ እባቡን ፡ ትረግጣለህ አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x) አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ ለዘላለም ፡ ኤልሻዳይ ፡ ነህ ፡ ና ፡ በፊቴ ፡ ተመላለስ የገባሁልህን ፡ ተስፋ ፡ አምጥቻለሁና ፡ ለአንተ ፡ በዚህ ስለዚህ ፡ አትጠራጠር ፡ ጸንተህ ፡ ቁም ፡ በእኔ ፡ ተማምነህ የማልጥል ፡ የማልተው ፡ አምላክ ፡ አለሁ ፡ እኔ ፡ በአጠገብህ አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x) አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ በሕይወትህ ፡ ዘመን ፡ ሁሉ ፡ ሊቋቋሙህ ፡ እንዳይችሉ ጠላቶችህን ፡ መታለሁ ፡ በፊት ፡ ለፊትህ ፡ ጥላለሁ በክንዶቼ ፡ ትያዛለህ ፡ ብቻ ፡ ታመን ፡ ትድናለህ ለዘላለም ፡ የእኔ ፡ ነህ ፡ ከእቅፌ ፡ ማን ፡ ሊያወጣህ አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x) አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ እንደቃሌ ፡ እንዲሁ ፡ ነኝ ፡ አደርጋለሁ ፡ ከቶ ፡ አልዋሽም የተናገርኩትን ፡ ሁሉ ፡ ፈጽማለሁ ፡ እንድ ፡ አይቀርም ከእኔ ፡ በቀር ፡ አምላክ ፡ የለም ፡ ማንም ፡ በምድር ፡ በሰማይ ብቻዬን ፡ ነኝ ፡ አልለወጥ ፡ ለዘላለም ፡ ኤልሻዳይ አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x) አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ እስራኤልን ፡ ትመራለህ ፡ ዮርዳኖስን ፡ ትከፍላለህ ከግራ ፡ ቀኝ ፡ አለሁ ፡ እኔ ፡ ታወጣለህ ፡ ታገባለህ ከአንተ ፡ ጋራ ፡ እንዳለሁኝ ፡ በህዝቡ ፡ ዘንድ ፡ ይታወቃል ዘመንህን ፡ ባርኬያለሁ ፡ ገለአድን ፡ ትወርሳለህ ከአንተ ፡ ጋር ፡ እንዳለሁኝ ፡ በህዝቡ ፡ ዘንድ ፡ ይታወቃል ዘመንህን ፡ ባርኬያለሁ ፡ ክብሬ ፡ በላይህ ፡ ይታያል አዝ፦ እንዲህ ፡ ላልከኝ ፡ ለአምላኬ እሰግዳለሁኝ ፡ ተንበርክኬ (፪x) አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የሕያዋን ፡ ተስፋ አስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አልጥልህም ፡ አልተውህም ፡ ላልከኝ ለዘላለም ፡ ከአንተ ፡ ጋር ፡ ነኝ ፡ ላልከኝ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የእስራኤል ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የቅዱሳን ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ የኢትዮጵያ ፡ ተስፋ እስግዳለሁ ፡ ዙፋንህ ፡ ይንሰራፋ