Loading
Singer
ያደረክልኝን ፡ ውለታ በምንም ፡ በምንም ፡ አልረሳም ከየት ፡ እንዳነሳኸኝ በምንም ፡ በምንም ፡ አልረሳም (፪x) ከትላንቱ ፡ ለሊት ፡ ካስፈሪው ከዚያ ፡ ከጨለማ ነጥቀህ ፡ ስታወጣኝ ፡ ኢየሱስ ማነው ፡ በዓይኑ ፡ ያላየ ማነው ፡ ጆሮው ፡ ያልሰማ ቁሻሻዬን ፡ ሸክሜን ፡ አራግፈህ ሰው ፡ ስታደርገኝ ያደረክልኝን ፡ ውለታ በምንም ፡ በምንም ፡ አልረሳም (፭x) መነሻ ፡ እንደሌለው ፡ መድረሻዬ ፡ ላይ ፡ ቆሜ የምሥጋና ፡ ቃሌን ፡ ለማጠፍ ፡ የረዳኝን ፡ ወዲያ ፡ ብዬ ከእናቴ ፡ ማህጸን ፡ ስወጣ ፡ በስኬት ፡ ካባ ፡ ተሽሜ ይህ ፡ ይመስል ፡ አልነካኝ ፡ ነፋሱ ፡ የማለፊያው ፡ የችግሬ እኔም ፡ እንዳልሆነ ፡ አላወራም ፡ ቆሜ ማን ፡ ረድቶኝ ፡ ማን ፡ አግዞኝ ፡ አልልም (፫x) ጉልበቴ ፡ አመጣልኝ ፡ አልልም (፫x) ጥበቤ ፡ በዝቶ ፡ እውቀቴ ፡ አልልም (፫x) ያከማቸሁት ፡ ይህ ፡ ሃብቴ ፡ አልልም (፫x) አላስብም ፡ እንደበረታሁ አላስብም ፡ ከእግዚአብሄር/ከፀጋው ፡ ውጪ አላስብም ፡ በጉብዝናዬ አላስብም ፡ አለፍኩት ፡ ብዬ (፪x) ከልጅነቴ ፡ እስከ ፡ እውቀቴ ያሳደከኝ ፡ ያስተማርከኝ (፪x) በፍቅር ፡ እጅህ ፡ አጉርሰኸኛል መምህሬ ፡ ነህ ፡ መች ፡ ይረሳኛል (፪x) ውጪውን ፡ አላየውም ፡ ላፍታ አልደሰት ፡ በግብዝ ፡ ትዝታ ገብቶኛል ፡ በቤቴ ፡ ያረከው አብዝተህ ፡ ለእኔ ፡ ያትረፈረፍከው (፪x) በእጄ ፡ ያለው ፡ ወርቅ ፡ አይሁንብኝ (፪x) አላቀለውም ፡ አይወድቅብኝም (፪x) በአንተ ፡ ጉያ ፡ ነው ፡ ዘላለሜ (፪x) ስምህ ፡ ሆንዋል ፡ የኑሮ ፡ አለሜ (፪x) ና ና ና ና ና ና (4) ውለታህ ፡(አልረሳም) ጥበቃህን ፡(አልረሳም) ምህረትን ፡ (አልረሳም) እኔ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም) ምህረትን ፡ (አልረሳም) ፍቅርህን ፡ (አልረሳም) ያረከውን ፡ (አልረሳም) ከቶ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም) አልረሳም ውለታህን ፡ (አልረሳም) ጥበቃህን ፡ (አልረሳም) ፍቅርህን ፡ (አልረሳም) እኔ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም) አሃ ፡ እኔ ፡ አልረሳም ፡ (አልረሳም) ዎዎው ፡ (አልረሳም) ኢየሱሴ ፡ (አልረሳም)