Loading
Singer
አቤቱ ፡ ለቀዳሚነትህ ፡ ጥንት ለኋላኛናትህ ፡ ፍጻሜ ፡ የለህ [፪x] አንተ ፡ እግዚአብሔር ፡ ነህ [፬X] አልፋ ፡ ኦሜጋ ፡ ፊተኛ ፡ ኋለኛ [፬X] ጌታ ፡ ዘመናትህ ፡ ዓማታትህ ፡ ቢቆጠሩ ፡ አያልቁም ለአንተ ፡ ምን ፡ ቢበዙ ፡ የዕድሜ ፡ ገደብ ፡ ከቶ ፡ አይችሉም ፡ ሊሰጡህ ዘመናትን ፡ አሳልፈህ ፡ አሳልፈህ አንተ ፡ ብቻ ፡ ትኖራለህ ፡ ትኖራለህ ዘላለማዊ ፡ ነህ ዘላለማዊ ፡ ነህ [፬X] አናልፍም ፡ ያሉ ፡ አለፉ አንሞትም ፡ ያሉትም ፡ ሞቱ ኃያላን ፡ ለአንተ ፡ ሰገዱ ኃይል ፡ የእግዚአብሔር ፡ ነው ፡ አሉ የአንተ፡ አልፋ ፡ የአንተ ፡ ኦሜጋ ሁሌ ፡ ጽኑ ፡ ነው ፡ መሽቶ ፡ ሲነጋ መንግስትህ ፡ ቋሚ ፡ ዘላለማዊ ሁሉ ፡ ሲያከትም ፡ አንተ ፡ ነህ ፡ ነዋሪ ዘላለማዊ ፡ ነህ ዘላለማዊ ፡ ነህ [፬X] ጌታ ፡ እግዚአብሔር ፡ ሆይ አንተ ፡ ያልነበርክበት ፡ ጊዜ ለቅጽበት ፡ አልነበረም ፡ አይኖርም ስልጣንህ ፡ መንግስትህ ፡ ነው ፡ ከዘላለም [፬x]