Loading
Singer
ወጣለሁ ፡ ገባለሁ ፡ በልዩ ፡ ጥበቃ ኢየሱሴን ፡ አልፎ ፡ ማነው ፡ እኔን ፡ ሚነካ አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም በጠላቴ ፡ ላልነካ ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x) ከአቤል ፡ ደም ፡ ይልቅ ፡ የሚናገር ፡ ደሙ እስከዛሬ ፡ ድረስ ፡ ትኩስ ፡ በመሆኑ የወረወርው ፡ ቀስት ፡ ፈልጎ ፡ አጥቶኛል የኢየሱሴ ፡ ደም ፡ በሙላት ፡ ጋርዶኛል ኃይል ፡ አለውና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x) ጋርዶኛልና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x) ወጣለሁ ፡ ገባለሁ ፡ በልዩ ፡ ጥበቃ ኢየሱሴን ፡ አልፎ ፡ ማነው ፡ እኔን ፡ ሚነካ አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም በጠላቴ ፡ ላልነካ ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x) ክፉ ፡ እንዲደሰት ፡ እንዲስቅ ፡ በእኔ ደግሶ ፡ እንዲበላ ፡ አይፈቅድም ፡ መድህኔ የቀባውን ፡ ሊያድን ፡ ይወጣል ፡ በግርማ አድኖኝ ፡ ስላየሁ ፡ እላለሁኝ ፡ ዘና ኃይል ፡ አለውና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x) ጋርዶኛልና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x) ወጣለሁ ፡ ገባለሁ ፡ በልዩ ፡ ጥበቃ ኢየሱሴን ፡ አልፎ ፡ ማነው ፡ እኔን ፡ ሚነካ አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም በጠላቴ ፡ ላልነካ ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x) ምክር ፡ ተመክሮብኝ ፡ መልክተኞች ፡ መጡ በክፉ ፡ ሴራቸው ፡ ህይወቴን ፡ ሊያጠምዱ ሰፈሬ ፡ ሲደርሱ ፡ አልቻሉም ፡ ሊቀርቡኝ በኢየሱሴ ፡ ደም ፡ ተሸፍኜ ፡ አዩኝ ኃይል ፡ አለውና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x) ጋርዶኛልና ፡ የኢየሱሴ ፡ ደም (፪x) አዝ፦ አልነካም ፡ አልነካም በጠላቴ ፡ ላልነካ ሸፍኖኛል ፡ የኢየሱስ ፡ ደም (፪x)