Loading
Singer
ይህንን ፡ ጌታ ፡ ነው ፡ ጌታዬ ፡ ነህ ፡ ያልኩት ጨለማውን ፡ አይቶ ፡ ልቡ ፡ የማይደነግጥ (፪x) የችሎቱ ፡ ብዛት ፡ እጅግ ፡ ይገርመኛል ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ና ፡ እንጂ ፡ ና ፡ ልጄ ፡ አትፍራ ፡ ይለኛል (፪x) አትፍራ ፡ ይለኛል አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x) አልመዝንህም ፡ ስለሆነና ፡ ስላልሆነ እምነቴ ፡ ዛሬም ፡ ትኩስ ፡ ነው ፡ መች ፡ ቀዘቀዘ አያሳልፍም ፡ እኔስ ፡ አልልም ፡ ውኃውን ፡ አይቼ ቀጥ ፡ ያለ ፡ መንገድ ፡ ይሆናል ፡ ስላለ ፡ ጐኔ አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x) በእኔ ፡ ውስጥ ፡ ያለው ፡ ይሄ ፡ ኢየሱስ ፡ መቼ ፡ ደክሞ ፡ ያውቃል ግራ ፡ አይገባው ፡ እንደ ፡ ሰው ፡ የት ፡ ይሸበራል ብቻ ፡ ከፊቴ ፡ ችግር ፡ ሲጋረጥ ፡ እንዲህ ፡ ይለኛል መፍትሄ ፡ የአንተ ፡ ነው ፡ ተሻገር ፡ እንጂ ፡ እረፍ ፡ ይለኛል አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x) ደመናን ፡ አይቶ ፡ ትንቢት ፡ መናገር ፡ ሁሉም ፡ ይችላል ንፋሱ ፡ ሲነፍስ ፡ ሰው ፡ ሁሉ ፡ ይዘንባል ፡ ይላል የእኛ ፡ ጌታ ፡ ግን ፡ ለየት ፡ ያለው ፡ ነው ፡ ትንቢት ፡ ሲናገር ውኃን ፡ ያመጣል ፡ እንዲሁ ፡ ደመና ፡ ሳይኖር አዝ፦ እስከሚሆን ፡ ድረስ ፡ ብቻ ፡ አላምንህም እስከመጨረሻው ፡ አትችልም ፡ አልልም ውኃውን ፡ እረግጠህ ፡ ማን ፡ ጀግና ፡ ና ፡ ይላል ከብዙ ፡ አማልክት ፡ የእኔ ፡ ጌታ ፡ ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል ፡ ለየት ለየት ፡ እኮ ፡ ይላል (፪x)