Loading
Singer
አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x) ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x) ማን ፡ ጠርቶ ፡ አፈረብህ ፡ አንገቱን ፡ ደፋብህ ቀና ፡ አልልም ፡ ብሎ ፡ ተሸማቀቀብህ እኔስ ፡ አላየሁም ፡ ከቶ ፡ አልሰማሁም ከፍ ፡ ከፍ ፡ አልኩ ፡ አንጂ ፡ አላሽቆለቆልኩም ሲወራ ፡ ሰምቼ ፡ ነበረ ፡ አሁን ፡ ግን ፡ ዓይኔ ፡ አይቷል ምሥጋናዬም ፡ ብሷል አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x) ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x) እርሱማ ፡ ሞኝ ፡ ነው ፡ ጊዜውን ፡ ይፈጃል ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲል ፡ ዕድሜውን ፡ ይገፋል ቢሉኝ ፡ ከሰነፎች ፡ መንደር ፡ አንዳንዶቹ እንግዲህ ፡ ማዳኑን ፡ ያያል ፡ ዓይናቹህ በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ ፡ በሰማይ ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት አለኝ ፡ በኢየሱስ ፡ ቤት አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x) ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x) ሞቅ ፡ ደመቅ ፡ ካሉ ፡ ከፈርዖን ፡ ቤት በንጉሠ ፡ ነገሥት ፡ ስልጣን ፡ ካለበት ጮማ ፡ ሲል ፡ ወይን ፡ ጠጅ ፡ ድሎት ፡ በሞላበት ብድራቱን ፡ ቆጥሮ ፡ ሙሴ ፡ አድርጓል ፡ ለቀቅ ለሁሉ ፡ እንደስራው ፡ ምትከፍል ፡ ነህና ፡ አምላኬ አረፈብህ ፡ ልቤ አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x) ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x) እርሱማ ፡ ሞኝ ፡ ነው ፡ ጊዜውን ፡ ይፈጃል ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ሲል ፡ ዕድሜውን ፡ ይገፋል ቢሉኝ ፡ ከሰነፎች ፡ መንደር ፡ አንዳንዶቹ እንግዲህ ፡ ማዳኑን ፡ ያያል ፡ ዓይናቹህ በምድር ፡ መቶ ፡ እጥፍ ፡ በሰማይ ፡ የዘለዓለም ፡ ሕይወት አለኝ ፡ በኢየሱስ ፡ ቤት አዝ፦ አልከሰርኩም ፡ አላፈርኩም ፡ አንተን ፡ አንተን ፡ ብዬ (፪x) ከትላንቱ ፡ ዛሬ ፡ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x) ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x) ብሷል ፡ ምሥጋናዬ (፫x) ብሷል ፡ ዝማሪዬ (፫x)