Loading
Singer
አዝ:- አንዳንዱ ፡ ንዋይ ፡ ፈልጐ ይሄዳል ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ለሚያልፈው ፡ ለሚጠፋው ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ሞኝ ፡ ነው ተራራ ፡ ሕይወት ፡ ዳገት ፡ ነው/መከራ ፡ ሕይወት ፡ ሰልፍ ፡ ነው ለመኖር ፡ ሁሌ ፡ ትግል ፡ ነው ቢሆንም ፡ ለተድላ ፡ ብዬ አልሄድም ፡ አማላኬን ፡ ጥዬ (፪x) አዝ:- አንዳንዱ ፡ ንዋይ ፡ ፈልጐ ይሄዳል ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ለሚያልፈው ፡ ለሚጠፋው ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ሞኝ ፡ ነው ሌሊት ፡ ላይ ፡ ፀሐይ ፡ እንድትወጣ ብፈልግ ፡ መች ፡ ይሆንና ለሁሉም ፡ ስርአት ፡ አለው እንስኪነጋ ፡ እጠብቃለሁ (፪x) አዝ:- አንዳንዱ ፡ ንዋይ ፡ ፈልጐ ይሄዳል ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ለሚያልፈው ፡ ለሚጠፋው ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ሞኝ ፡ ነው እግዚአብሔር ፡ ለእኔ ፡ ያስቀመጠውን ለማንም ፡ እንደማይሰጠው ገብቶናል ፡ ተረድቻለሁ እርሱን ፡ ትቼ ፡ የት ፡ እሄዳለሁ (፪x) አዝ:- አንዳንዱ ፡ ንዋይ ፡ ፈልጐ ይሄዳል ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ለሚያልፈው ፡ ለሚጠፋው ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ሞኝ ፡ ነው አልከዳውም ፡ ይሄን ፡ ሳወራ ሞራልም ፡ አይደል ፡ ፉከራ ከልቤ ፡ እወደዋለው ያለ ፡ እርሱ ፡ እንዴት ፡ እኖራለሁ (፪x) አዝ:- አንዳንዱ ፡ ንዋይ ፡ ፈልጐ ይሄዳል ፡ አምላኩን ፡ ትቶ ለሚያልፈው ፡ ለሚጠፋው ይሄ ፡ ሰው ፡ እንዴት ፡ ሞኝ ፡ ነው