Loading
Singer
በረሃብ ፡ ቀጠና ፡ አይደለሁም ፡ እኔ ልምላሜ ፡ ረግፎ ፡ አልገደለኝ ፡ ጠኔ በአረንጓዴው ፡ ገነት ፡ ምንጭ ፡ በሚፈልቅበት እንድኖር ፡ ተፈርዷል ፡ በኢየሱስ ፡ ዳኝነት አዝ፦ አልሻም ፡ ከአንተ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም (፪x) አልፈልግም ፡ ዳግም አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ) ለምንድን ፡ ነው ፡ አሉኝ ፡ ክርስትያን ፡ የሆንከው ሁልጊዜ ፡ ኢየሱስ ፡ ኢየሱስ ፡ ምትለው እስቲ ፡ ልንገራችሁ ፡ ይህንን ፡ ሚስጥር . (2) . ፡ አይሎ ፡ ነው ፡ የመስቀሉ ፡ ፍቅር አዝ፦ አልሻም ፡ ከአንተ/ከእርሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም (፪x) አልፈልግም ፡ ዳግም አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ) ነፍሴ ፡ አዋጅ ፡ ሰምታ ፡ የሞትን ፡ ቀጠሮ ፍጥረት ፡ ሲያወራ ፡ የሽንፈት ፡ እሮሮ ሕይወት ፡ ያበዛልኝ ፡ ማነው ፡ ከተባለ አዳኙ ፡ ኢየሱስ ፡ ነው ፡ በዙፋኑ ፡ ያለ አዝ፦ አልሻም ፡ ከእርሱ ፡ ውጭ ፡ ብልጭልጩን ፡ ዓለም በቅቶታል ፡ ያልቤ ፡ አልፈልግም ፡ ዳግም (፪x) አልፈልግም ፡ ዳግም አልፈልግም ፡ ዳግም (እምቢ) እስግዲህ ፡ በኢየሱስ ፡ ተደላድያለሁ ዓለም ፡ የማይሰጠውን ፡ ሰላም ፡ አግኝቻለሁ ታዲያ ፡ ለምን ፡ ልሩጥ ፡ ለምን ፡ ልቅበዝበዝ እስቲ ፡ በኢየሱስ ፡ ላይ ፡ እርፍ ፡ ልበል እርፍ ፡ እርፍ ፡ እርፍ ፡ እርፍ ፡ ድግፍ ጥግት ፡ ጥግት